ኢትዮጵያ ቡሩንዲን በደርሶ መልስ አሸንፋ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈች
ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ዓለም ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ማጣሪያ ኢትዮጵያ ቡሩንዲን በደርሶ መልስ አሸንፋ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፋለች።
የመልስ ጨዋታውን በዛሬው እለት ቡጁንቡራ ላይ ያከናወነው ብሔራዊ ቡድኑ 2ለ1 አሸንፏል።
የኢትዮጵያን የማሸነፊያ ጎሎች ምኅረት አየለ እና ሊዲያ እያሱ ከመረብ አሳርፈዋል።
በአሰልጣኝ ራውዳ አሊ የሚመራው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የሁለተኛ ዙር የማጣሪያ ጨዋታውን በድምር ውጤት 4ለ2 አሸንፎ ወደ መጨረሻው እና 3ኛው ዙር ማጣሪያ ተሻግሯል።
ኢትዮጵያ የሦስተኛ ዙር የማጣሪያ ጨዋታዋን ከዲሞክራቲክ ኮንጎ እና ከዛምቢያ አሸናፊ ጋር ትጫወታለች።
ኢትዮጵያ በ3ኛው ዙር ድል የሚቀናት ከሆነ በሞሮኮ አስተናጋጅነት ወደ ሚካሄደው ከ17 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ የምታልፍ ይሆናል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ አስፈረመ
ማንቸስተር ዩናይትድ አንድሬ ሳንቶስን አስፈረመ
የ2018 የCBE የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በማሸነፍ ሁለት ዋንጫ ላነሳው የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ክልሉ ያዘጋጀውን የዕውቅናና የሽልማት ፕሮግራም ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 06/2018 ከቀኑ 12፡00 ጀምሮ በሀዋሳ ሀይሌ ሪዞርት ይካሄዳል።