ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡናን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ
ሀዋሳ፡ ጥር 14/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ 16ኛ ሳምንት መጨረሻ መርሐግብር ግብር ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡናን 3 ለ 0 በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል።
ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ከሁለት ተከታታይ የአቻ ውጤት በኋላ ሲዳማ ቡና ወደ አሸናፊነት ተመልሷል።
በአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ ለሚመራው ሲዳማ ቡና የማሸነፊያ ጎሎችን ብለስ ናጎ ፣ ፍራኦል መንግስቱ እና ዮሴፍ ዮሐንስ አስገኝተዋል።
9ኛ የሊግ ድሉን ያሳካው ሲዳማ ቡና ነጥቡን 33 በማድረስ ከተከታዩ ሀዋሳ ከተማ በአምስት ነጥብ ርቆ ሊጉን እየመራ ይገኛል።
7ኛ የሊግ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና በአንፃሩ በ19 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
“ማንቸስተር ሲቲ በዚህ አጨዋወት ሊጉን ማሸነፍ አይችልም”ፖል ሜርሰን
ኬሮድ የጎዳና ላይ ሩጫ ህዝብ ለህዝብ የሚያስተሳስርና አንድነታችንን ይበልጥ የምናጠናክርበት በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ
ከ1500 በላይ ኤሊት አትሌቶች የሚሳተፉበት 6ኛው ዙር የኬሮድ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ ተጀመረ