ማንቸስተር ሲቲ ማርክ ጉሂን ለማስፈረም ተስማማ
ማንቸስተር ሲቲ ማርክ ጉሂን ለማስፈረም ከስምምነት ላይ መድረሱ ተገልጿል።
ማንቸስተር ሲቲ እንግሊዛዊውን የመሀል ተከላካይ ለማስፈረም ከፓላስ ጋር በመርህ ደረጃ መስማማቱን ቢቢሲ አስነብቧል።
ማንቸስተር ሲቲ ከጉሂ ጋር በግል ጉዳይ ከስምምነት ላይ ባይደርስም ተጫዋቹን ለማሳመን ላይቸገር ይችላል ተብሏል።
የክርስቲያል ፓላሱ አሰልጣኝ ኦሊቨር ግላስነር ተጫዋቹ ማንቸስተር ሲቲን ለመቀላቀል ከጫፍ መድረሱን ተናግረዋል።
ሲትዝኖቹ የ25 ዓመቱን ተጫዋች ለማስፈረም 20 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ ማቅረባቸው ተዘግቧል።
ዘጋቢ ፡ በሙሉቀን ባሳ

More Stories
“ማንቸስተር ሲቲ በዚህ አጨዋወት ሊጉን ማሸነፍ አይችልም”ፖል ሜርሰን
ኬሮድ የጎዳና ላይ ሩጫ ህዝብ ለህዝብ የሚያስተሳስርና አንድነታችንን ይበልጥ የምናጠናክርበት በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ
ከ1500 በላይ ኤሊት አትሌቶች የሚሳተፉበት 6ኛው ዙር የኬሮድ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ ተጀመረ