የ1447ኛው ዓመተ ሂጅራ የሀጅ ምዝገባ ጥር 18 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ የሲዳማ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አስታወቀ
ከአምስቱ የእስልምና መሰረቶች አንዱ ሀጅ ነው ያሉት የሲዳማ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝደንት ሸህ አብዱሽኩር፤ ኢኮኖሚያዊና ጤናዊ አቅም በፈቀዱለት የእስልምና ላይ ሁሉ ግዴታ የተደረገ የአምልኮ ስርዓት መሆኑንም ገልፀዋል።
በዚህም በየአመቱ ከ3 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ሙስሊሞች የሀጅ ተግባር እንደሚፈፅሙ የተናገሩት ሀላፊው፤ ዘንድሮ የተፈቀደልንን 43 ሺህ ሙስሊሞችን የማሳተፍ እድል ለመጠቀም ምዝገባ እያካሄድን እንገናኛለን ነው ያሉት።
ይሁንና በዚህ አመት የምዝገባው ጊዜ ቀድሞ በመጀመሩ ሙስሊምች በወቅቱ መጥተው እየተመዘገቡ አይደለም ያሉት ሸህ አብዱ ሽኩር፤ የምዝገባ ጊዜው ጥር 18 ቀን 2018 ዓ.ም ስለሚጠናቀቅ በእነዚህ ጊዜያት መመዝገብ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ዘጋቢ፡ ሰብስቤ አደም

More Stories
መሬት ውስን የተፈጥሮ ሀብት በመሆኑ በአግባቡ በመምራትና ከብክነት በመጠበቅ ቀጣይነት ያለዉን ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
መስቀል የድህነት ምልክት መሆኑን የካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮና ምዕራብ ኦሞ አህጉረ-ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ህዝቅኤል ተናገሩ