ኮቢ ሜይኑ ማንቸስተር ዩናይትድን መልቀቅ ይፈልጋል
እንግሊዛዊው አማካይ ኮቢ ሜይኑ የልጅነት ክለቡን ማንቸስተር ዩናይትድ መልቀቅ እንደሚፈልግ ተገልጿል።
ኮቢ ሜይኑ በማንቸስተር ዩናይትድ በቂ የሚባል የመጫወቻ ጊዜን እያገኘ ባለመሆኑ በጥር የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ክለቡን ለቆ በውሰት ወደ ሌላ ክለብ ለማምራት መዘጋጀቱን ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።
የ20 ዓመቱ ተጫዋች በያዝነው የውድድር ዘመን በሊጉ አንድም ጨዋታን በቋሚነት አለመጀመሩ ይታወቃል።
ስለኮቢ ሜይኑ ከመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጥያቄ የቀረበላቸው አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም “መቼ የመጫወት ዕድል እንደሚያገኝ አላውቅም” ሲሉ ምላሽ ሰጥቷል።
የቀድሞ የማንቸስተር ዩናይትድ ዝነኛ ተጫዋች ፖል ስኮልስ ከሰሞኑ ሜይኑ ክለቡን ቢለቅ ለዕሱ የተሻለ እንደሚሆን ሀሳብ መስጠቱ ይታወሳል።
ኮቢ ሜይኑ ከ3 ዓመታት በፊት ለማንቸስተር ዩናይትድ ዋናው ቡድን ተሰልፎ መጫወት መጀመሩ አይዘነጋም።
የክለቡ አካዳሚ ውጤት የሆነው ኮቢ ሜይኑ እስካሁን ለቀያይ ሰይጣኖች በ82 ጨዋታዎች ተሰልፎ ከመጫወት ባሻገር 7 ጎሎችን በስሙ አስመዝግቧል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
አርሰናል በአስቶንቫላ ተሸነፈ
በመላ አፍሪካ ርዕሰ ከተሞች መካከል፣ ለዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲና የጋራ አህጉራዊ ተቋማት ማዕከል በሆነችው ምድራችን፣ ታላቅ የሚዲያ መድረክ ማስተናገድ ታላቅ ኩራት ነው – የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
አሌክሳንደር አርኖልድ ለሁለት ወራት ከሜዳ የሚያርቀውን ጉዳት አስተናገደ