ክርስቲያኖ ሮናልዶ በነጩ ቤተመንግስት ተከስቷል
የ5 ጊዜ የባሎንዲኦር አሸናፊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በነጩ ቤተመንግስት ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ተገናኝቷል።
በቤተመንግስቱ ለፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ለሳውዲ አረቢያው ልዑል ሙሀመድ ቢን ሰልማን የእራት ግብዣ መደረጉ ተገልጿል።
የእራት ግብዣ ያደረጉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በመገኘቱ ምስጋና አቅርበዋል።
ፕሬዝዳንቱ አስከትለውም “ሮናልዶ የምንጊዜም ምርጡ እግር ኳስ ተጫዋች ነው” በማለት ተናግረዋል።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በቅርቡ ከእንግሊዛዊው ጋዜጠኛ ፒርስ ሞርጋን ጋር በነበረው ቆይታ ዶናልድ ትራምፕን አግኝቶ ማነጋገር እንደሚፈልግ ገልፆ ነበር።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
በ31 ተከታታይ ጨዋታዎች ያልተሸነፈው ብሔራዊ ቡድን
ወደ ዓለም ዋንጫው ለበርካታ ጊዜ በማለፍ ከብራዚል በመቀጠል ሁለተኛው ሀገር
ጋብርኤል ማጋሌሽ የጡንቻ ጉዳት እንዳጋጠመው ተገለፀ