አሽራፍ ሀኪሚ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመረጠ
ሞሮኳዊው የመስመር ተከላካይ አሽራፍ ሀኪሚ የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል።
አሽራፍ ሀኪሚ የመጨረሻ እጩ ሆነው የቀረቡትን ሞሐመድ ሳላን እና ቪክቶር ኦሲምሄን በመብለጥ ነው የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን ያሸነፈው።
የፒኤስጂው ተጫዋች በ2024/25 የውድድር ዓመት ያሳየው ድንቅ ብቃት ለዚህ ሽልማት አብቅቶታል።
የ27 ዓመቱ ተጫዋች በውድድር ዓመቱ ውስጥ ከፈረንሳዩ ክለብ ጋር የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ፣ የአውሮፓ ሱፐር ካፕ፣ የፍሬንች ሊግ ኣ እና የኮፕ ዴ ፍራንስ ዋንጫዎችን ማሳካት ችሏል።
ከዚህም ባሻገር የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን ወደ 2026 የዓለም ዋንጫ ስታልፍ ከፍተኛ ድርሻ ተወጥቷል።
አሽራፍ ሀኪሚ ሙስጠፋ ሀጂ እንደ አውሮፓውያኑ በ1998 የዓመቱ ምርጥ ሽልማትን ካሸነፈ በኋላ ይህንን ሽልማት ያሸነፈ የመጀመሪያው ሞሮኳዊ ተጫዋች መሆን ችሏል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
በዘመናዊ መንገድ ንብ የማነብ ስራ በመጀመር ውጤታማ መሆናቸውን በወላይታ ዞን የዳሞት ወይዴ ወረዳ ወጣቶች ተናገሩ
የማታ 1፡00 ዜና 24፤ ሀዋሳ፡ ሕዳር 08/2018 ዓ.ም
የማታ 1፡00 ዜና 24፤ ሀዋሳ፡ ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም