ጋብርኤል ማጋሌሽ የጡንቻ ጉዳት እንዳጋጠመው ተገለፀ
የአርሰናል የመሀል ስፍራ ተከላካይ በቀኝ እግሩ ጡንቻ ላይ ጉዳት እንዳጋጠመው ተገልጿል።
ጋብርኤል ማጋሌሽ ብራዚል ከሴኔጋል ጋር ባካሄደችው የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ጉዳት ማስተናገዱ ይታወሳል።
የመድፈኞቹ የኋላ ደጀን የጡንቻ ጉዳት እንዳጋጠመው መረጋገጡን ተከትሎ በፈረንሳይ ሊል ብራዚል ከቱኒዚያ ጋር ማክሰኞ ዕለት ከምታደርገው ሌላኛው የወዳጅነት ጨዋታ ውጪ ሆኗል።
ጋብርኤል ማጋሌሽ አርሰናል በቀጣይ ከቶትንሃም፣ ባየር ሙኒክ እና ቼልሲ ጋር በሚያከናውናቸው ወሳኝ ጨዋታዎች ላይሰለፍ እንደሚችል ተነግሯል።
የ27 ዓመቱ ተጫዋች አርሰናል በዘንድሮው የውድድር ዓመት በፕሪሚየር ሊጉ በ11 ጨዋታዎች 5 ጎሎች ብቻ ተቆጥሮበት በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ አናት ላይ እንዲቀመጥ ጉልህ አስተዋጽኦ ከማበርከቱ ባሻገር ሁለት ወሳኝ ጎሎችን ከመረብ አሳርፏል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ናይጀሪያ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ ከዓለም ዋንጫ ውድድር ውጪ ሆነች
ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ መድህንን በማሸነፍ ደረጃውን አሻሻለ
በእንግሊዝ ታላላቅ ክለቦች የሚፈለገው ካሪም አድዬሚ ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት ተጣለበት