ናይጀሪያ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ ከዓለም ዋንጫ ውድድር ውጪ ሆነች
የ3 ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ናይጀሪያ ከሁለት ተከታታይ የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ውጪ ሆናለች።
ናይጀሪያ ትናንት ምሽት በአፍሪካ አህጉር የዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ በዲሞክራቲክ ኮንጎ በመለያ ምት ተሸንፋ ወደ ውድድሩ ማለፍ ሳትችል ቀርታለች።
በሞሮኮ የተካሄደው የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ መደበኛው 90 ደቂቃው እና ጭማሪው 30 ደቂቃ 1 አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው የመለያ ፍፁም ቅጣት ምት ግን ዲሞክራቲክ ኮንጎ ናይጀሪያን 4ለ3 አሸንፋለች።
ውጤቱን ተከትሎ ዲሞክራቲክ ኮንጎ አፍሪካን በመወከል በኢንተርኮንፌደሬሽን ጥሎ ማለፍ ጨዋታ የምትካፈል ይሆናል።
ዲሞክራቲክ ኮንጎ በዚህ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ድል የሚሆናት ከሆነ እንደ ፈረንጆቹ ከ1974 በኋላ ወደ ዓለም ዋንጫው ትመለሳለች።
ናይጀሪያ በአንፃሩ በ22ኛው እና 23ኛው የዓለም ዋንጫ ማጣሪዎችን ማለፍ አልቻለችም።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ጋብርኤል ማጋሌሽ የጡንቻ ጉዳት እንዳጋጠመው ተገለፀ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ መድህንን በማሸነፍ ደረጃውን አሻሻለ
በእንግሊዝ ታላላቅ ክለቦች የሚፈለገው ካሪም አድዬሚ ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት ተጣለበት