ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ መድህንን በማሸነፍ ደረጃውን አሻሻለ
በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ 2ኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ መድህንን በማሸነፍ ደረጃውን አሻሽሏል።
ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ የወቅቱ የሊጉን ሻምፒዮን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ነው ያሸነፈው።
የቅዱስ ጊዮርጊስን ብቸኛ የማሸነፊያ ጎል ንጋቱ ገብረስላሴ በ18ኛው ደቂቃ በራሱ መረብ ላይ አሳርፏል።
በአሰልጣኝ ገብረመድህን ሃይሌ የሚመራው ኢትዮጵያ መድህን በዚህ የውድድር ዓመት የመጀመሪያ ሽንፈቱን ነው ያስተናገደው።
ቅዱስ ጊዮርጊስ በፕሪሚዬር ሊጉ ኢትዮጵያ መድህንን ለ20ኛ ጊዜ ማሸነፍ ችሏል።
በ2018 የውድድር ዓመት 4ኛ የሊግ ድሉን ያሳካው ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥቡን 12 በማድረስ ከሲዳማ ቡና በግብ ክፍያ አንሶ 2ኛ ደረጃን በመያዝ የአዲስ አበባ ከተማ ቆይታውን አጠናቋል።
ኢትዮጵያ መድህን በበኩሉ በ5 ነጥብ በፕሪሚዬር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 11ኛ ላይ ይገኛል።
ዘጋቢ ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
በእንግሊዝ ታላላቅ ክለቦች የሚፈለገው ካሪም አድዬሚ ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት ተጣለበት
የባርሴሎና ቀዳሚ ተመራጭ
ጤናማ እና አምራች ዜጋን ለመፍጠር በጤና ስፖርት ቡድኖች የሚሳተፍ ማህበረሰብ መገንባት ወሳኝ መሆኑን የጎፋ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ገለጸ