በእንግሊዝ ታላላቅ ክለቦች የሚፈለገው ካሪም አድዬሚ ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት ተጣለበት
ሀዋሳ፡ ሕዳር 07/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የቦሩሲያ ዶርትሙንዱ የፊት መስመር ተጫዋች ካሪም አድዬሚ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘቱ ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት ተጥሎበታል።
ካሪም አድዬሚ እና ባለቤቱ ሎሬዳና ዜፊ ከአንድ ዓመት በፊት ሁለት ህገወጥ የጦር መሳሪያዎችን ይዛችኋል በሚል ከጀርመን ፖሊስ ክስ ቀርቦባቸው ነበር።
ለወራት በተጫዋቹ ላይ ምርመራ ሲያደርግ የቆየው የጀርመን ፖሊስ አድዬሚ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት ጥሎበታል።
እንደ ቢልድ መረጃ መሰረት በጀርመናዊው ተጫዋች ላይ በ60 ቀናት ውስጥ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ የ450 ሺህ ፓውንድ የገንዘብ ቅጣት ተጥሎበታል።
የ23 ዓመቱ ካሪም አድዬሚ በአማካይ ሲሰላ በቀን 7 ሺህ 500 ፓውንድ የገንዘብ ቅጣት ይከፍላል እንደማለት ነው።
በቦሩሲያ ዶርትሙንድ እስከ 2027 ድረስ የሚያቆየው ኮንትራት ያለው አድዬሚን ለማስፈረም አርሰናል፣ ማንቸስተር ዩናይትድ እና በቼልሲ በጥብቅ እንደሚፈልጉት በመዘገብ ላይ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ መድህንን በማሸነፍ ደረጃውን አሻሻለ
የባርሴሎና ቀዳሚ ተመራጭ
ጤናማ እና አምራች ዜጋን ለመፍጠር በጤና ስፖርት ቡድኖች የሚሳተፍ ማህበረሰብ መገንባት ወሳኝ መሆኑን የጎፋ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ገለጸ