ዎልቭስ ሮብ ኤድዋርድስን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ
የእንግሊዙ ክለብ ዎልቭስ ሮብ ኤድዋርድስን አዲስ አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን አሳውቋል።
በዚህ ዓመትም ደካማ አጀማመርን በማድረግ ላይ የሚገኘው ክለቡ ከ10 ቀናት በፊት ፖርቹጋላዊውን አሰልጣኝ ቪቶር ፔሬራን ከሃላፊነት ማሰናበቱ ይታወሳል።
በተሰናባቹ አሰልጣኝ ምትክ የቀድሞ የተካላካይ ስፍራ ተጫዋቹን ሮብ ኤድዋርድስን ከሻምፒዮንሺፑ ክለብ ሚድልስብሮው በማምጣት ሾሟል።
የ42 ዓመቱ አሰልጣኝ በዎልቭስ ቤት ለ3 ዓመት ከመንፈቅ የሚያቆያቸውን ኮንትራት ተፈራርመዋል።
ዎልቭስም ለዌልሳዊው አሰልጣኝ የውል ማፍረሻ 3 ሚሊዮን ፓውንድ ለሚድልስብሮው መክፈሉን ስካይ ስፖርት አስነብቧል።
ባለፈው ሰኔ ወር የሚድልስብሮው ዋና አሰልጣኝ ሆነው የተቀጠሩት ኤድዋርድስ ክለቡን በሻምፒዮን ሺፑ በአሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ ከሚመራው ኮቬንትሪ ሲቲ በ5 ነጥብ አንሶ 2ኛ ደረጃ ላይ እንዲገኝ አስችሏል።
ዎልቭስ በአንፃሩ ዘንድሮ በፕሪሚዬር ሊጉ ከ11 ጨዋታዎች መካከል በዘጠኝ ጨዋታዎች ተሸንፎ በ2 ነጥብ ብቻ በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ በመቀመጥ አስካፊ ጅማሮን በማድረግ ላይ ነው።
ከዚህ ቀደም ሉተን ታውንን በፕሪሚዬር ሊጉ መርተው ወደ ታችኛው ሊግ ያወረዱት ሮብ ኤድዋርድስ ተኩላዎቹን ወደ ውጤታማነት እንዲመልሱት ሀላፊነት ተሰጥቷቸዋል።
አሰልጣኝ ሮብ ኤድዋርድስ በተጫዋችነት ዘመኑ እንደ አውሮፓውያኑ ከ2004 እስከ 2008 ድረስ በዎልቭስ 111 ጨዋታዎችን በመሃል ተከላካይነት ተሰልፎ አከናውኗል።
በዎልቭስ አሰልጣኝነት የመጀመሪያ ጨዋታውን በፕሪሚዬር ሊጉ ከክርስቲያል ፓላስ ጋር ከ10 ቀናት በኋላ የሚያደርግ ይሆናል።
ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ማንቸስተር ሲቲ የፊል ፎደን ውል ለማራዘም ስራ መጀመሩ ተገለፀ
በኢትዮጵያ ዋንጫ ቤንች ቡና ማጂ፣አርባምንጭ ከተማ፣ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ እና ኢትዮጵያ መድህን ወደ ቀጣዩ ዙር አለፉ
ኦስካር በልብ ህመም ምክንያት ሆስፒታል መግባቱ ተሰማ