ኦስካር በልብ ህመም ምክንያት ሆስፒታል መግባቱ ተሰማ
ሀዋሳ፡ ሕዳር 03/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የቀድሞ የቼልሲ የመሀል ሜዳ ተጫዋች ኦስካር በልብ ህመም ምክንያት ሆስፒታል መግባቱ ተሰምቷል።
ብራዚላዊው ተጫዋች በሀገሩ ሊግ ለአዲሱ የውድድር ዓመት በትናንትናው ዕለት የተክለ ሰውነት ምርመራ በሚደረግለት ወቅት በድንገት መታመሙ ነው የተገለጸው።
በአሁኑ ሰዓት እየተጫወተ የሚገኝበት ሳኦፖሎ እንዳስታወቀው ኦስካር ህመሙ እንዳጋጠመው በቶሎ ወደ ሆስፒታል መወሰዱን አሳውቋል።
ተጫዋቹ በአሁኑ ሰዓት በተረጋጋ የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም አስታውቋል።
ኦስካር ባጋጠመው ህመም ምክንያት በ34 ዓመቱ እግርኳስ መጫወትን ለማቆም ሊገደድ እንደሚችል ግሎቦ ስፖርት አስነብቧል።
ኦስካር በእንግሊዙ ክለብ ቼልሲ እንደ አውሮፓውያኑ ከ2012 እስከ 2017 ድረስ ለአምስት ዓመታት ተጫውቶ ማሳለፉ ይታወሳል።
ከምዕራብ ለንደኑ ክለብ ጋር ሁለት የፕሪሚዬር ሊግ ዋንጫዎችን ማንሳት ችሏል።
በማስከተል ወደ ቻይና አምርቶ በሻንጋይ ፖርት ሰባት ዓመታትን ቆይታ ካደረገ በኋላ ነበር በ2024 ለልጅነት ክለቡ ሳኦፖሎ የፈረመው።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ዎልቭስ ሮብ ኤድዋርድስን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ
በኢትዮጵያ ዋንጫ ቤንች ቡና ማጂ፣አርባምንጭ ከተማ፣ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ እና ኢትዮጵያ መድህን ወደ ቀጣዩ ዙር አለፉ
አንጎል ሦስት የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾችን ከለከለች