አንጎል ሦስት የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾችን ከለከለች

አንጎል ሦስት የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾችን ከለከለች

አፍሪካዊቷ ሀገር አንጎላ ሦስት የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ወደ ግዛቷ እንዳይገቡ ክልከላ ጥላለች።

የአንጎላ ብሔራዊ ቡድን ከአርጀንቲና አቻው ጋር  ከቀናት በኋላ የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚያደርግ ማሳወቁ ይታወሳል።

የነፃነት ቀኗን አስታካ ትልቅ የወዳጅነት ጨዋታ ያዘጋጀችው አንጎላ ግን የቢጫ ወባ ክትባታቸውን ያላጠናቀቁ ቁልፍ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ላይ ወደ ሉዋንዳ እንዳይመጡ ክልከላ መጣሏ ተገልጿል።

እነዚህም የተከለከሉ ተጫዋቾች የአትሌቲኮ ማድሪዶቹ ጁሊያን አልቫሬዝ፣ናሁኤል ሞሊና እና ጁሊያኖ ሲሚዮኔ ናቸው።

አንጎላ የወዳጅነት ጨዋታውን ለማከናወን አርጀንቲና የጠየቀችውን 12 ሚሊዮን ዮሮ እንደምትከፍል ተነግሯል።

በወዳጅነት ጨዋታው ላይ የ8 ጊዜ የባሎንዲኦር አሸናፊው ሊዮኔል ሜሲ በአልቢሴሌስቴዎች ስብስብ ተካቷል።

ጨዋታው ኅዳር 5/2018 ዓ.ም ሉዋንዳ በሚገኘው ኖቬምበር 11 ስታዲየም የሚካሄድ ይሆናል።

ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ