ቼልሲ በሰንደርላንድ ሲሸነፍ ኒውካስል ፉልሃምን አሸነፈ

ቼልሲ በሰንደርላንድ ሲሸነፍ ኒውካስል ፉልሃምን አሸነፈ

በ9ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ቼልሲ በሜዳው በሰንደርላንድ  ሲሸነፍ ኒውካስል ዩናይትድ ፉልሃምን አሸንፏል።

በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም አዲስ አዳጊውን ሰንደርላንድ ያስተናገደው ቼልሲ ከመምራት ተነስቶ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

በጨዋታው አሌሃንድሮ ጋርናቾ በ4ኛው ደቂቃ ጎል አስቆጥሮ የምዕራብ ለንደኑን ክለብ ቀዳሚ ማድረግ ችሎ ነበር።

ሆኖም ግን ዊልሰን ኢሲዶር እና ታልቢ ለጥቋቁር ድመቶች ጎል አስቆጥረው ክለባቸው ወሳኝ ድል እንዲያሳካ አስችለዋል።

ሰንደርላንድ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን 17 በማድረስ 2ኛ ደረጃን ይዟል።

በዚህ ዓመት 3ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቼልሲ በበኩሉ በ14 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ኒውካስል በአንፃሩ በሜዳው ፉልሃምን አስተናግዶ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ለማግፓይሶቹ የድል ግቦችን ጃኮብ መርፊ እና ብሩኖ ጊውማሬሽ አስገኝተዋል።

ፉልሃምን ከሽንፈት ያልታደገችውን ጎል ደግሞ ሳሳ ሉኪች አስቆጥሯል።

ኒውካስል ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን 12 በማድረስ 11ኛ ደረጃን መያዝ ሲችል 5ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ፉልሃም በበኩሉ በ8 ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ፕሪሚዬር ሊጉ ምሽት ላይ መካሄዱን ሲቀጥል ማንቸስተር ዩናይትድ በኦልድትራፎርድ ስታዲየም ብራይተንን ከ1 ሰዓት ጀምሮ ያስተናግዳል።

እንዲሁም ምሽት 4 ሰዓት ላይ ብሬንትፎርድ ከሊቨርፑል ይጫወታሉ።

ዘጋቢ ፡ ሙሉቀን ባሳ