በኮሬ ዞን የአስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች መልሶ የማደራጀት ምክክር መድረክ ተካሄደ

‎‎

‎መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሬ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ እና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ሳሙኤል ሳዲሁን የደሞዝ ማሻሻያው ሰው ተኮር በመሆኑ በአሠሪው መሥሪያ ቤቶች አመራርና ፋይናንስ አካላትን ባሳተፈ መልኩ የጋራ ምክክር ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

‎‎

‎የኮሬ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ፣ የግብርና መምሪያ ኃላፊና የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አስታረቀኝ አንደባ እንደተናገሩት አመራሩ ሁልጊዜ ዝግጁ መሆን እንዳለበት አስታውሰው የመዋቅር ስፋትና ጥበት በየጊዜው እየተጠና ችግሮች እየተፈታ ይሄዳል በማለት በዋናነት ወጪ ቆጣቢ አገልግሎት ለህብረተሰቡ መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል።

‎በመድረኩም ከደሞዝና የውሎ አበል ማሻሻያ ጋርም በተያያዘ ኢኮኖሚን በጥረት ሠርቶ ማምጣት እንደሚጠበቅ አስረድተዋል፡፡

‎ከተሳታፊዎች መካከል አቶ አለማየሁ አሰፋ፣ አቶ ወረደ ወርቁና ሌሎችም በሰጡት አስተያየት በደሞዝ ማሻሻያ ትግበራ የሲቪል ሰርቪስና ሰው ሀብት በጥንቃቄ መሥራትና የአመራሩም ክትትል እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።

‎ዘጋቢ፡ ምርጫ መላኩ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን