የበጎ አገልግሎት ተግባር ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመርዳት መልካም ዕድል የፈጠረ ነው::
የደቡብ ኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ያስገነባውን የአቅመ ደካሞች ቤት የርክክብ መርሃግብር አካህዷል፡፡
የቢሮው ሠራተኞች ከወር ደመወዛቸው ባሰባሰቡት ገንዘብና ድጋፍ ከሌሎች አካላት ጋር በመቀናጀት የቤት መስሪያ ቁሳቁሶችን በመግዛት በጥራት መገንባቱን የገለፁት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አብዮት መብራቱ (ዶ/ር) ናቸው፡፡
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመርዳት መልካም ዕድል የፈጠረ መሆኑን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ፥ ኢንስቲትዩቱ የቤት ቁሳቁሶችን ከማሟላት ባለፈ በቤተሰቡ ያሉትን ልጆች ለማስተማር ድጋፍ ማድረጋቸውን አብራርተዋል።
በዲላ ከተማ ከ300 በላይ ቤቶች በክረምቱ በመገንባት ለችግር ተጋላጭ ለሆነ የማህበረሰብ ክፍሎች ማስረከባቸውን የተናገሩት የዲላ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ መንግስቱ ተክሌ የክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ሠራተኞች ጥራቱን የጠበቀ ቤት በአጭር ጊዜ ግንባታውን አጠናቀው በማስረከባቸው አመስግነዋል፡፡
መልካምን ማድረግ የእርስ በእርስ ግንኙነትን የሚያጠናክር ነው፤ በአቅራቢያችን ጧሪና ጠያቅ ለሌላቸው የኑሮ ውድነት ጫና እያለ ከጉድለታችን መደገፍ መንፈሳዊ እርካታን የፈጠረ ነው ያሉት የኢንስቲትዩቱ ዕቅድ በጀት ክትትልና ግምገማ ግብረ መልስ ሥራ ሂደት ዳይሬክተር አቶ ፋንታሁን ዮናስ ናቸው፡፡
የለውጡ መንግሥት ባለፋት ዓመታት በርካታ ሰው ተኮር የልማት ሥራዎችን በመሥራት የህብረተሰቡን ችግር እያቃለለና ሁለተናዊ ልማት እያስመዘገበ እንደሚገኝ አቶ ፋንታሁን ጠቅሰዋል፡፡
ድጋፍ የተደረገላቸው እናቶችም የዘመናት እንባቸው ስለታበሰ የኢንስቲትዩቱን ሠራተኞችና ኃላፊዎችን አመስግነዋል፡፡
ዘጋቢ: ውብሸት ኃ/ማርያም – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
ከ98 ሚሊዮን ብር በላይ የውስጥ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
የህፃናትን ጤናማነት ለመጠበቅ ከቅድመ ወሊድ ክትትል ጀምሮ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
በኮሬ ዞን የአስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች መልሶ የማደራጀት ምክክር መድረክ ተካሄደ