የቡርጂ ዞን ምክር ቤት አቶ ትንሳኤ ዮሐንስ ወጌ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመ

የቡርጂ ዞን ምክር ቤት አቶ ትንሳኤ ዮሐንስ ወጌ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመ


ሀዋሳ፡ ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የቡርጂ ዞን ምክር ቤት ባካሄደው 5ኛ ዙር 3ኛ የሥራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አቶ ትንሳኤ ዮሐንስ ወጌን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ በሙሉ ድምጽ ተቀብሎ አጽደቀ።
‌‎
‎የቡርጂ ዞን ም/ቤት አፌ ጉባኤ ወ/ሮ ወለቱ ዋዮ ምክር ቤቱ በህገ መንግስቱ የተሰጠውን ስልጣን መሠረት በማድረግ በተጠራው አስቸኳይ ጉባኤ የም/ቤቱ አባላት የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ ጠይቀዋል።

‎የ2017 የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ አጀንዳ በሙሉ ድምፅ የፀደቀ ሲሆን የክልሉ መንግስት ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ለምክር ቤቱ የቡርጂ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በእጩነት የቀረቡትን አቶ ትንሳኤ ዮሐንስ ወጌ የቡርጂ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው እንዲመሩ በሙሉ ድምፅ አፀድቋል።

‎የቡርጂ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙት አቶ ትንሳኤ ዮሐንስ በም/ቤቱ ፊት ቀርበው ዞኑን በቅንነት እና በታማኝነት ለማገልገል ቃለ መሐላ ፈጽመዋል።

‎በጉባኤው ከክልል፣ ከዞን፣ ከወረዳ እና ከከተማ አስተዳደር የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግለዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተሳትፈውበታል ።

‎ዘጋቢ: ወርቅአገኘሁ ወልደየስ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን