የባስኬቶ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ አመት የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን አካሂዷል

ምክር ቤቱ በነበረው ቆይታ የዞኑን ዋና አስተዳዳሪ ሹመት መርምሮ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል።

የባስኬቶ ዞን ህዝብ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ማርቆስ ልፋቱ፤ ጉባኤው የህዳሴ ግድባችን ተጠናቆ አገልግሎት መሥጠት በጀመረበት ማግስት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዱፄ ታምሩ፤ ዞኑን በዋና አስተዳዳሪነት እንዲያገለግሉ እጩ ዶ/ር ሳሙኤል ደሳለኝን በዕጩነት ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

የምክር ቤቱ አባላት በቀረቡት ዕጩ አስተዳዳሪ ዙሪያ ሀሳብ አስተያየታቸውን ሰጥተው በሙሉ ድምፅ አፅድቀዋል።

የባስኬቶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እጩ ዶ/ር ሳሙኤል ደሳለኝ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ባደረጉት ንግግር በዞኑ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሠላምና ጸጥታ ዘርፎች ላይ የታቀዱ ተግባራትን ለማሳካት በፅናት ይሰራል ብለዋል።

በዞኑ የሚገኘውን እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ጥቅም ላይ ለማዋል ያለ ልዩነት አካታች አሰራርን ለመከተል ልዩ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን አረጋግጠዋል።

ዘጋቢ: አወል ከድር – ከሳውላ ጣቢያችን