በቫሌንሽያ ግማሽ ማራቶን አትሌት ዩሚፍ ቀጄልቻ አሸነፈ

በቫሌንሽያ ግማሽ ማራቶን አትሌት ዩሚፍ ቀጄልቻ አሸነፈ

በስፔን ቫሌንሽያ በተካሄደው በወንዶች የግማሽ ማራቶን አትሌት ዩሚፍ ቀጄልቻ አሸንፏል።

አትሌት ዩሚፍ ቀጄልቻ 58 ደቂቃ ከ02 ሴኮንድ በመግባት ነው ውድድሩን በቀዳሚነት ያጠናቀቀው።

የርቀቱ የዓለም ክብረወሰን ባለቤት የሆነው አትሌት ዮሚፍ የባለፈው ዓመት የቫሌንሽያ ግማሽ ማራቶን ውድድርም አሸናፊ እንደነበር ይታወሳል።

በሴቶች የግማሽ ማራቶን ውድድር ደግሞ አትሌት ፎቲዬን ተስፋዬ 2ኛ ሆና አጠናቃለች።

አትሌቷ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 1 ሰዓት ከ05 ደቂቃ ከ11 ሴኮንድ ፈጅቶባታል።

ውድድሩን ኬንያዊቷ አትሌት አግኔስ ንጌቲች በቀዳሚነት አጠናቃለች።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ