በሮዱዋ ደርቢ ሲዳማ ቡና ሀዋሳ ከነማን አሸነፈ
በ2ኛ ሳምንት የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ በተካሄደው የሮዱዋ ደርቢ ሲዳማ ቡና ሃዋሳ ከነማን በማሸነፍ ተከታታይ ድል አስመዝግቧል።
ከቀኑ 10 :00 ጀምሮ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም የተካሄደው የወንድማማቾች ደርቢ በሲዳማ ቡና 1ለ0 አሸናፊነት ነው የተጠናቀቀው።
የሲዳማ ቡናን የማሸነፊያ ጎል አምበሉ ያሬድ ባየህ 52ኛው ደቂቃ ላይ በፍፁም ቅጣት ከመረብ አሳርፏል።
2ኛ ተከታታይ ድሉን ያሳካው ሲዳማ በ6 ነጥብ በፕሪሚዬር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ አናት ላይ መቀመጥ ችሏል።
በቀጣይ የሊጉ መርሐግብር ሀዋሳ ከተማ ከወላይታ ድቻ እንዲሁም ሲዳማ ቡና ከፋሲል ከነማ በተመሳሳይ ረቡዕ ዕለት የሚጫወቱ ይሆናል።
ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ቼልሲ በሰንደርላንድ ሲሸነፍ ኒውካስል ፉልሃምን አሸነፈ
ሊቨርፑል፣ ቼልሲ፣ ሪያል ማድሪድና ባየርን ሙኒክ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ
ሃኪም ዚዬች ወደ ዋይዳድ ካዛብላንካ ለመዛወር ተስማማ