ሊቨርፑል፣ ቼልሲ፣ ሪያል ማድሪድና ባየርን ሙኒክ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የ3ኛ ዙር የመጨረሻ ቀን ጨዋታ ሊቨርፑል፣ ቼልሲ፣ ሪያል ማድሪድና ባየርን ሙኒክ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል።
ወደ ጀርመን አምርቶ ፍራንክፈርትን የገጠመው ሊቨርፑል ከመመራት ተነስቶ 5ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት በመርታት ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል።
የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች ሁጎ ኤኪቲኬ በቀድሞ ክለቡ ላይ፣ ቨርጂል ቫንዳይክ፣ ኢብራሂማ ኮናቴ፣ ኮዲ ጋክፖ እና ዶሚኒክ ዦቦዥላይ ከመረብ አሳርፈዋል።
በሜዳው አያክስን ያስተናገደው ቼልሲም 5ለ1 በሆነ ተመሳሳይ ውጤት የሆላንዱን ክለብ አሸንፏል።
ለምዕራብ ለንደኑ ክለብ የድል ጎሎችን ማርክ ጉይ፣ ኤንዞ ፈርናንዴዝ፣ ኤስታቫኦ፣ ካይሴዶ እና ጆርጅ አስቆጥረዋል።
ሪያል ማድሪድ እንዲሁ በሳንቲያጎ ቤርናቢዩ ከዩቬንቱስ ጋር ተጫውቶ 1ለ0 አሸንፏል።
የሎስብላንኮዎቹን ወሳኝ የድል ጎል ጁድ ቤሊንግሀም አስገኝቷል።
የጀርመኑ ክለብ ባየርንሙኒክ በሜዳው ክለብ ብሩጅን ገጥሞ 4ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት ረቷል።
ለባቫሪያኑ ክለብ የድል ጎሎችን ካርል፣ ሀሪ ኬን፣ ሉይዝ ዲያዝ እና ኒኮላስ ጃክሰን ከመረብ አሳርፈዋል።
በሌሎች ጨዋታዎች አትሌቲክ ቢልባኦ ቃራባግን እንዲሁም ጋላታሳራይ ቦዶ ግሊምትን በተመሳሳይ 3ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።
ስፖርቲንግ ሊዝበን በበኩሉ በሜዳው አሸሎምፒክ ማርሴን 2ለ1 ማሸነፍ ችሏል።
ሞናኮ ከቶትንሃም ያከናወኑት ጨዋታ ደግሞ ያለ ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
ሃኪም ዚዬች ወደ ዋይዳድ ካዛብላንካ ለመዛወር ተስማማ
የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት ነገ መካሄድ ይጀመራል
43 ጎሎች 5 ቀይ ካርዶች እንዲሁም 6 የፍፁም ቅጣት ጎሎች በአንድ ምሽት