አርሶ አደሩ በእንሰት ተክል የምግብ ዋስትናውን በማረጋገጥ የኢኮኖሚ አቅሙን እንድያሳድግ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
ሀዋሳ፣ ጥቅምት 15/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ)በአሪ ዞን ዎባ አሪ ወረዳ አርሶ አደሩ የእንሰት ተክልን በማልማት ከዘርፉ ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆን ስልጠና ተሰጥቷል
የትኛውንም የአየር ንብረት ለውጥ የመቋቋም ከፍተኛ አቅም ያለው የእንሰት ተክል በዎባ አሪ ወረዳ በየአመቱ ከ180 ሄ/ር በላይ በአዲስ ተከላ እንደሚለማ የገለፁት የወረዳዉ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቢሻዉ መካሪ ከሙሩፅ ጎይቶም የእሸት ቡና መፈልፈያ ኢንድስትሪ ባለቤት ጋር በመተባበር አርሶ አደሩ በአከባቢዉ ካለዉ ሰፊ የእንሰት ምርት በኢኮኖሚ አቅማቸዉን እንዲያሳድጉ ለሴት አርሶ አደሮች ስልጠናዉ መሰጠቱን ገልፀዋል፡፡
የሙሩፅ ጎይቶም የእሸት ቡና መፈልፈያ ኢንድስትሪ ኃላፊ አቶ ማሙሽ አልዬ በበኩላቸዉ አከባቢዉ ላይ ካለዉ የእንሰት ዝርያ የተሻለ የእንሰት ዝርያን ከምዕራብ አሪሲ በማምጣትና አከባቢዉ ላይ በማልማት አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰሩ እንዳለ አስረድተዋል፡፡
የዎባ አሪ አርሶ አደሮች የእንሰት ተክልን ከአምቾና ከቂጣ ባለፈ የተለያዩ የምግብ ዓይነቶችን አዘጋጅተው ለራሳቸው ምግብነትም ሆነ ለገበያ አቅርበው በመሸጥ ተጠቃሚ እንዲሆን ስልጠና መሰጠቱን ተገልጿል፡፡
በወረዳዉ የዲራመርና የቦይካ ቀበሌ አርሶ አደር ሚሚ ስዩምና ገሺዬ ዳሽዬ በጋራ በሰጡት አስተያየት ከዚህ ቀደም እንሰቱን በመቆፈር ተፍቆ ቂጣ ብቻ እንደሚያዘጋጁና አሁን ግን በስልጠናዉ ቡላና ሌሎች የምግብ አዘገጃጀቶችን ግንዛቤ በማግኘታቸዉ በቀጣይ በዘርፉ በተሻለ ሁኔታ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ ፡ በናወርቅ መንግስቱ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
የሃገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገትን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር በሚደረገው ጥረት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ
ህብረት ሥራ ማህበራት ለሀገር ብልፅግና መሪ ተዋናይ ናቸው ሲል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የህብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ ገለፀ
በክራምት ወራት ሲከውኑት የነበረውን የበጎ ተግባር በበጋ ወራት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በስልጤ ዞን የሁልባረግ ወረዳ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ተናገሩ