ሃኪም ዚዬች ወደ ዋይዳድ ካዛብላንካ ለመዛወር ተስማማ
የቀድሞ የቼልሲ የፊት መስመር ተጫዋች ሃኪም ዚዬች የሞሮኮውን ክለብ ዋይዳድ ካዛብላንካን ለመቀላቀል ከስምምነት ላይ መድረሱ ተገልጿል።
የ32 ዓመቱ ተጫዋች በነፃ ዝውውር የሀገሩን ክለብ ለመቀላቀል መስማማቱን የፋብሪዚዮ ሮማኖ መረጃ ያስረዳል።
ሃኪም ዚዬች ሦስት የውድድር ዓመታትን በምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ቆይታ ካደረገ በኋላ ወደ ቱርክ አቅንቶ ለጋላታሳራይ መፈረሙ ይታወሳል።
ተጫዋቹ ባለፈው የውድድር ዓመት በኳታሩ ክለብ አል ዱሀይል ተጫውቶ ካሳለፈ በኋላ ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ በሰኔ ወር ቡድኑን ለቆ ያለክለብ ቆይቷል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው