በኢትዮጵያ ውስጥ እየተገነቡ ከሚገኙ 18 ለኤክስፖርት የሚቀረቡ እንስሳት ማቆያ ማዕከላት መካከል ሁለቱ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን በበናፀማይ ወረዳና በቱርሚ ከተማ በ6 ወራት ውስጥ የሚጠናቀቅ የግንባታ ፕሮጀክት ርክክብ ተደርጓል።
በሀገራችን ኢትዮጵያ 1 መቶ 15 ሚሊዮን ዶላር በጀት በኦሮሚያ፣ በሱማሊያ፣ በአፋር፣ በደቡብ ኢትዮጵያና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች ከዘርፉ አርብቶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል የእንስሳት ገበያ ማዕከላት ግንባታ እንደሚገነባ ተገልጿል።
የአደጋ ስጋት ቅነሳና አካታች የኢኮኖሚ እሴት ማሻሻያ ፕሮጀክት (DRIVE) መሃንዲስ ኢንጂነር አዳነ መንገሻ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የDRIVE ፕሮጀክት አስተባባሪ ዶ/ር ስዩም መታፈሪያ፤ እስካሁን ፕሮጀክቱ የእንሰሳት ጤና ኬላዎች የእንስሳት ክሊኒኮችና የእንስሳት ገበያ ማዕከሎችን እየገነባ ማቆየቱን ገለጸው በዛሬው ዕለትም በደቡብ ኦሞ ዞን በበናፀማይ ወረዳና ቱርሚ ከተማ አስተዳደር በ1 መቶ 39 ሚሊዮን ብር ለኤክስፖርት የሚሆኑ እንስሳት መሰብሰቢያ ማዕከላት ግንባታ ለማስጀመር ለሥራ ተቋራጭ የማስረከብ ሂደት ላይ ነው ብለዋል።
በሀገራችን ኢትዮጵያ 13 የቄራ ማዕከላት ብቻ መኖራቸውን የጠቆሙት የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች፤ ረጂም ኪሎ ሜትሮችን ስለሚጓዙ ለውጭ ኤክስፖርት በሚፈለገው ደረጃ ለማቅረብ ያለውን ውስንነት ለመቅረፍና የእንስሳት ሃብቱን በአግባቡ ለመጠቀም በማለም የሚሰራ ፕሮጀክት ነው ብለዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የእንሰሳት ጤናና ግብአት አቅርቦት ዘርፍ ኃላፊ አዲሱ እዮብ (ዶ/ር)፤ በአርብቶ አደሩ ኋላቀር የእንሰሳት እርባታ ከነበረበት ወደ ዘመናዊ እርባታ ለማሸጋገር የዘመነ የገበያ ሰንሰለት መኖር እንደሚያስፈልግ አንስተው የፕሮጀክቱ መጀመር የኢኮኖሚ ምንጩ የእንስሳት ሀብት የሆነውን አርብቶ አደሩን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ መሆኑን ተናግረዋል።
ምክትል ቢሮ ኃላፊና የእንሰሳት ጤናና ግብአት አቅርቦት ዘርፍ ኃላፊ አዲሱ እዮብ (ዶ/ር) አክለውም፤ እንስሳት ረጅም ርቀት ሳይጓዙ በአቅራቢያ መሰብሰቡ ለኤክስፖርት ውጤታማነት ላይ ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ኘሮጀክቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ የክልሉ መንግሥት በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ ምክትል የቢሮ ኃላፊና የልዩ ድጋፍ ማስተባበሪያና መሠረተ ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አይዴ ሎሞዶ፤ ኘሮጀክቱ ለአካባቢው ማህበረሰብ ሰፊ ዕድሎች መምጣቱን አንስተው ሥራ ተቋራጩና አካባቢውን የማስተዳደር ሚናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አሳሰበዋል።
የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ በበኩላቸው፤ የዞኑ አርበቶ አደር ከእንስሳት ሀብቱ ተጠቃሚ እንዲሆንና የእንስሳት ሀብቱን ለኤክስፖርት ምቹ ለማድረግና የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ኘሮጀክቱ የጀመረውን ግንባታ ሂደት የዞኑ መንግሥት በአስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ አመልክተዋል።
በዞኑም የበናፀማይ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ዮሐንስ ጋርሾ በበኩላቸው፤ እንደወረዳ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶናል፤ ሥራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ክትትልና በቅርበት ተቀናጅተን እንሰራለን ሲሉ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።
የሥራ ተቋራጩ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዳዳቻ ጃርሶ በአካባቢው ያለው ዕድልና ችግሮች በጥልቀት በመገንዘብ እንደ ዜጋ የበኩሌን እወጣለሁ ኘሮጀክቱን በተባለው ጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ በቁርጠኝነት እንዲሚሰራ ተናግረዋል።
ዘጋቢ: ጄታ ታገሠ – ከጂንካ ጣቢያችን
አርብቶ አደሩን ከእንስሳት ሀብት ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ የእንስሳት ኤክስፖርት ማዕከላት እንደሚያስፈልጉ ተጠቆመ

More Stories
በጌዴኦ ዞን የጤና መድህን አባል የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የይርጋ ጨፌ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽህፈት ቤት አስታወቀ
ሃኪም ዚዬች ወደ ዋይዳድ ካዛብላንካ ለመዛወር ተስማማ
የተሻለ የሥራ አፈጻጸም ያስመዘገቡ አካላት መበረታታት እና ዕውቅና መስጠት በባለሙያዎች መካከል የተሻለ መነሳሳት እንደሚፈጠር ተገለፀ