በጌዴኦ ዞን የጤና መድህን አባል የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የይርጋ ጨፌ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽህፈት ቤት አስታወቀ

ጽህፈት ቤቱ የ2017 በጀት ዓመት ማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን (ማህጤመ) ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት አባላትን የማፍራት የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።

‎የማህጤመ ዓላማ መደጋገፍን እና መተባበርን መሰረት ያደረገ መሆኑን የተናገሩት የከተማው ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳዊት ጉሚ፤ በ2017 በጀት ዓመት በዘርፉ የተቀመጡ ዓላማዎችን ከማስፈጸም አኳያ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።

በከተማው የጤና መድህን አባል የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ መሆኑንም ኃላፊው ጠቁመዋል።

‎አክለውም በ2016 በጀት ዓመት 53 በመቶ የነበረውን የአባላት ምጣኔ በ2017 በጀት ዓመት 67 በመቶ ማድረስ መቻሉን በመጠቆም፤ በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት በበጀት ዓመቱ ከ13 ሺህ በላይ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ወጪ በተለያዩ ደረጃዎች የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን ተናግረዋል።

‎የይርጋ ጨፌ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ታደለ ጥላሁን በበኩላቸው፤ በዘርፉ እየተሰጠ ካለው አገልግሎት የተነሳ ከዚህ ቀደም ከነበረው አሁን ላይ በህብረተሰቡ የግንዛቤ ለውጥ እየታየ መምጣቱን በመጠቆም በቀጣይ የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል።

‎የይርጋ ጨፌ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ወዶ በበኩላቸው፤ መንግሥት በሽታን ቀድሞ መከላከል እና አክሞ ማዳን በሚል መርህ የዜጎችን ጤና ለመጠበቅ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን በመጠቆም በአቅም ውስንነት ምክንያት የህክምና አገልግሎት የማግኘት አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አባል በመሆን የህክምና አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረጉ ረገድ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል።

‎በመድረኩ የ2017 በጀት ዓመት የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን በበጀት ዓመቱ አባላት የማፍራት የንቅናቄ መድረኩ በጊዜ አለመካሄዱ፣ የተሰበሰበውን ገንዘብ በጊዜ ወደ ቋት ከማስገባት እና መረጃ በአግባቡ ከማደራጀት አኳያ ውስንነቶች እንደነበሩ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

‎በመጨረሻም የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን የመክፈል አቅምን መሰረት ያደረገ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን መዋጮ አከፋፈል ማስፈጸሚያ ማንዋል በተመለከተም ገለጻ ተደርጓል።

‎በመድረኩ የየሴክተር መስሪያ ቤት ኃላፊዎች፣ የከተማ ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን፣ ጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች፣ የይርጋ ጨፌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ ደረጀ ማሞ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

‎ዘጋቢ፡ እንግዳየሁ ቆሳ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን