የተሻለ የሥራ አፈጻጸም ያስመዘገቡ አካላት መበረታታት እና ዕውቅና መስጠት በባለሙያዎች መካከል የተሻለ መነሳሳት እንደሚፈጠር ተገለፀ

የተሻለ የሥራ አፈጻጸም ያስመዘገቡ አካላት መበረታታት እና ዕውቅና መስጠት በባለሙያዎች መካከል የተሻለ መነሳሳት እንደሚፈጠር ተገለፀ

የኣሪ ዞን ደቡብ ኣሪ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቭስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በዕቅድ አፈጻጸም የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ተቋማት እና ፈጻሚዎች እውቅናና ሽልማት መርሃ ግብር አካሄዷል ።

በመረሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወረዳው የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ እና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ዮናስ አልቅሻ እንደተናገሩት በፐብሊክ ሰርቭሱ አፈጻጸም ላይ የተሻሉ ሆነው የተገኙ ግለሰቦች እና ተቋማት መሸለምና ማበረታታት ወሳኝና መሠረታዊ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

የወረዳዉ ፐብሊክ ሰርቪስ የሰዉ ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሳህሉ ታምሩ በየአመቱ አፈጻጸም በመገምገም ላቅ ያለ ተግባራትን ለሰሩ ፈፃሚ ግለሰቦች የማበረታቻ የእዉቅናና የሽልማት ፕሮግራም መዘጋጀቱ ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም የተሻለ አፈጻጸም በማስመዝገብ የእውቀትና ሽልማት ካገኙት መካከል አቶ አዲሱ ቡርዝዳቦ ወ/ሮ ሰላም ተሻገር የሜዳልያ እና የምስክር ወረቀት ማግኘት መቻላቸው ከማስደሰትም በላይ ይበልጥ እንዳነሳሳቸው ገልጸዋል።

ዘጋቢ፡ ጳውሎስ አሚገሮ – ከጂንካ ጣቢያችን