የደቡብ መንገዶች ባለስልጣን ጂንካ ዲስትሪክት በበኩሉ በአከባቢው ያለው የአየር ሁኔትና ናዳ ችግሩን እንዳባባሰው አመላክተዋል ።
አስተያየታቸውን የሰጡን አካላት የመንገዱ መበላሸት ከማህበራዊ ህይወታቸው ባለፈ ለአላስፈላጊ ወጪዎች በመዳረግ በኢኮኖሚያቸውም ላይ ተፅዕኖ በመፍጠሩ መንግስት ለመንገዱ ዘላቂ መፍትሄ እንዲፈልግላቸው ጠይቀዋል፡፡
የወባ ኣሪ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መምህሩ ጌታቸው መንገዱ የኣሪ ዞኑን ከወባ አሪና ሰሜን አሪ ጋር የሚያገናኝ ብቸኛው መንገድ መሆኑን ጠቅሰው፥ በአከባቢው የተከሰተው ናዳ በመንገዱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማስከተሉ ችግሩንም ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር እየተሰራ ነው ብለዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ አቶ ሊየው ካሳሁን በበኩላቸው ከማህበረሰቡ የተነሳው ቅሬታ አግባብነት ያለው መሆኑን ጠቁመው፥ በአከባቢው ያለው የዝናብ ሁኔትና ናዳ ችግሩን እንዳባባሰው አድጎታል ብለዋል።
ችግሩንም ለመቅረፍ በቀጣይ ጥናቶች ተደርገው ዘላቂ መፍትሄ እስኪፈጠር ድረስ እንቅስቃሴዎች እንዳይቛረጡ ማሽኖችን በማስገባት ጊዜያዊ መፍትሄ ለመስጠት ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።
ዘጋቢ፡ በናወርቅ መንግስቱ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
መሬት ውስን የተፈጥሮ ሀብት በመሆኑ በአግባቡ በመምራትና ከብክነት በመጠበቅ ቀጣይነት ያለዉን ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
መስቀል የድህነት ምልክት መሆኑን የካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮና ምዕራብ ኦሞ አህጉረ-ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ህዝቅኤል ተናገሩ