እንሰት ለምግብ ዋስትና አለኝታና ተፍቆ ለምግብነት የሚዉል ወሳኝ የጤንነት መጠበቂያ፣ የጥንካሬ መሰረት ተደርጎ የሚወሰድና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የዳዉሮ ዞንን ጨምሮ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች በስፋት የሚመረት ተክል ነዉ።
የዳዉሮ ዞን ቆዳ ስፋት ከ4 መቶ 44 ሺህ በላይ ሄክታር ሲሆን 4ቱ ከተማ አስተዳደሮችና 10ሩም ወረዳዎች ለእንሰት ምርት ተስማሚ የአየር ሁኔታ ያላቸዉ ሲሆኑ በእነዚህ መዋቅሮች ከ3 ሚሊየን በላይ ፍንካች በመቅበር ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊና የአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ምትኩ ለይኩን ገልፀዋል።
አቶ ምትኩ አክለዉም፤ የእንሰት ተክል ለም አፈር በንፋስና በጎርፍ ታጥቦ እንዳይወስድ የመከላከል አቅሙ ከፍተኛ እንደሆና ከዚህም ባሻገር የአፈር ለምነትን እና እርጥበት ጠብቆ በማቆየት ለምርታማነት ዕድገት ከፍተኛ አአስተዋጽኦ እንዳለዉ ተናግረዋል፡፡
እንዲሁም ኮባው (ቅጠሉ) እንደ ዳቦ ለመሳሰሉት ምግብ ማብሰያና ለተለያዩ የግብርና ዉጤቶች መጠቅለያነት ግልጋሎት ይውላል ብለዋል።
ከእንሰት ተረፈ ምርቶች የመቀመጫና የወለል ምንጣፎችን ጨምሮ በርካታ መገልገያዎች ስለሚሠራ ከዳዉሮ ብሔረሰብ ጋር ያለውን ቁርኝት ዘመን ተሻጋሪ ያደርገዋል ሲሉም ተናግረዋል።
እንሰት የምግብ ዋስትና መረጋገጥ ጉልህ አስተዋፅኦ ከመኖሩም አልፎ ለሰውና ለእንስሳት ከተለያየ በሽታ የመከላከልና ከጉዳት ለማገገም የሚያስችል መድኃኒት አገልግሎት የሚዉል ተክል እንደሆነ በማረቃ ዌዳ ኢየሱስ ቀበለ በዘርፉ ጥናት ያደረጉ አቶ አንባዪ ታደሰ ገልፀዋል።
ከ1 መቶ 8 በላይ የእንሰት ዝሪያዎች እንዳሉ የገለፁት አቶ አምባዬ ለአብነትም ማዚያ፣ ሾዶድኒያ፣ ያቃ፣ አርኪያ እና ሱይቲያ ጠቅሰዉ በርካታ ዝሪያዎች ለመድኃኒትነት እንደሚዉሉም አስረድተዋል።
በዞኑ ካሉት ለእንሰት ምርት ተስማሚ ወረዳዎች መካከል አንዱ የማረቃ ወረዳ ሲሆን በሽታን መቋቋም የሚችልና ቶሎ ልደርስ የሚችል የእንሰት ዝሪያ ለማባዛትና የአርሶ አደሩን የሞግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የተለያዩ ማህበራትና ሠርቶ ማሳያዎችን በመጠቀም ዝሪያ የማባዛት ሥራዎች በትኩረት እየሰሩ መሆናቸዉን በወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የአርሻ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ጦፉ ተናግረዋል።
እንሰት ከዳዉሮ ብሔረሰብ ጋር ከጥንት ጀምሮ ጥብቅ የሆነ ቁርኝት እንዳለዉ የገለፁት አቶ ሙሉቀን የእንሰት ተክል የሚፈለገውን ምርትና ውጤት እንዳይሰጥ ከሚያደርጉ ተግዳሮቶች መካከል ዋነኞቹ የአጠውልግና የአምቾ አበስብስ በሽታ፣ ፍልፈልና ጃርት እንዳያጠቃ አርሶ አደሩ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበትም አሳስበዋል።
ከእንሰት ተዋፅኦዎች መካከል ተፍቆ ቡላ ተዘጋጅቶ ለልጆችና ለአዋቂዎች ጤና ተስማሚ ሲሆን ገንፎ እንዲሁም ባጭራ ለምግብነትና ለመባያነት ከሚውሉት ተጠቃሽ መሆናቸዉን እንሰት ሲፍቁ ካገኘናቸዉ አናቶች መካከል ወ/ሮ እታገኘዉ ደጀኔና አበዛሽ ኃይሌ ገልፀዋል።
ዘገባ፡ አባይነሽ ወራቦ – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
ባመረቱት ምርት የምግብ ዋስትናቸውን ከማረጋገጥ አልፎ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ወረዳ አርሶ አደሮች ተናገሩ
ግራሃም ፖተር የሲዊዲን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ በመሆን ተሾሙ
የፌደሬሽን ምክር ቤት እና ተጠሪ ተቋማት በካፋ ዞን ሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ለአቅመ-ደካሞች ያስገነቧቸውን መኖሪያ ቤቶች እያስረከቡ ነው