በቺሊ አስተናጋጅነት በመካሄድ ላይ በሚገኘው 24ኛው ከ20 ዓመት በታች አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ ፈረንሳይ አሸንፋ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በውድድር መድረኩ ለፍፃሜ አልፋለች።
በቫልፓይራሶ የተደረገው የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች የግማሽ ፍፃሜ መርሐግብር መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ እና ጭማሪው 30 ደቂቃ 1 አቻ በሆነ ውጤት ነበር የተጠናቀቀው።
አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው የመለያ ፍፁም ቅጣት የአትላስ አንበሳዎቹ 5ለ4 አሸንፈው ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ዋንጫው ፍፃሜ በመድረስ አስደናቂ ታሪክ ሰርተዋል።
በውድድር መድረኩ ከ20 ዓመታት በኋላ ለግማሽ ፍፃሜ መድረስ የቻሉት የአትላስ አንበሳዎቹ በምድብ ማጣሪያው ስፔንን እና ብራዚልን በማሸነፍ ቀዳሚ ሆነው ከምድባቸው ወደ ጥሎ ማለፉ መሻገራቸው ይታወሳል።
በጥሎ ማለፉ ደቡብ ኮሪያን 2ለ1 ሲያሸንፉ በሩብ ፍፃሜው ደግሞ አሜሪካን 3ለ1 አሸንፈው በጠንካራ ብቃት ነው ወደ ግማሽ ፍፃሜው የተሻገሩት።
ሞሮኮ በፊፋ ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ለፍፃሜ በመድረስ ከናይጄሪያ እና ጋና በመቀጠል 3ኛዋ አፍሪካዊት ሀገር መሆን ችላለች።
በሌላ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ አርጀንቲና ኮሎምቢያን 1ለ0 አሸንፋ ወደ ፍፃሜው ተሻግራለች።
በፍፃሜውም ሞሮኮ የውድድሩን ዋንጫ 6 ጊዜ በማንሳት ቀዳሚ ከሆነችው አርጀንቲና ጋር እሁድ ሌሊት ትፋለማለች።
ፈረንሳይ ከኮሎምቢያ ደግሞ ለደረጃ ቅዳሜ ዕለት ከምሽቱ 4 ሰዓት ጀምሮ የሚጫወቱ ይሆናል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
ማንቸስተር ዩናይትድ የካስሜሮን ውል ለማራዘም ማጤን ጀመረ
ሞሮኮ ወደ ፍፃሜ ለማለፍ ዛሬ ምሽት ከፈረንሳይ ጋር ትጫወታለች
ክብረወሰኖች የሚከተሉት ተዓምረኛ