ማንቸስተር ዩናይትድ የካስሜሮን ውል ለማራዘም ማጤን ጀመረ

ማንቸስተር ዩናይትድ የካስሜሮን ውል ለማራዘም ማጤን ጀመረ

የእንግሊዙ ክለብ ማንቸስተር ዩናይትድ የመሐል ሜዳ ተጫዋቹን ካስሜሮን ኮንትራት ለማራዘም ማጤን መጀመሩ ተገልጿል።

ብራዚላዊው አማካይ አሁን ላይ በቀያይ ሴይጣኖቹ ቤት ያለው ኮንትራት በዚህ ዓመት መጨረሻ የሚጠናቀቅ ቢሆንም ዩናይትድ ግን ተጫዋቹን ለተጨማሪ ዓመት የማቆየት ፍላጎት እንዳለው ዴይሊ ሜይል አስነብቧል።

ማንቸስተር ዩናይትድ ግን የ32 ዓመቱ ተጫዋች ውሉን የሚያራዝም ከሆነ አሁን እየከፈለ ከሚገኘው ደሞዝ መቀነስ የሚያስችል ቅድመ ሆኔታ ማስቀመጡን ዘገባው አመላክቷል።

በ2022 ከሪያል ማድሪድ ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ የተዛወረው ካስሜሮ በእንግሊዙ ክለብ በሳምንት 375 ሺህ ፓውንድ እየተከፈለው ይገኛል።

የአምስት ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው ካስሜሮ በማንቸስተር ዩናይትድ እስካሁን 131 ጨዋታዎችን አከናውኖ 18 ጎሎችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ