ሞሮኮ አሜሪካን በማሸነፍ ለግማሽ ፍፃሜ ደረሰች
በቺሊ አስተናጋጅነት በመካሄድ ላይ በሚገኘው ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ አሜሪካን በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ደርሳለች።
ሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር በሩብ ፍፃሜ ጨዋታ አሜሪካን 3ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ነው ወደ ግማሽ ፍፃሜው የተሻገረችው።
ለአትላስ አንበሳዎቹ ወሳኝ የድል ግቦችን ፉአድ ዛሆኒ፣ ጆሹዋ ዋይንዴር በራሱ ላይ እና ጄሲም ያሲን ከመረብ አሳርፈዋል።
ሞሮኮ በቀጣይ ወደ ፍፃሜ ለማለፍ ከፈረንሳይ ጋር የምትፋለም ይሆናል።
ፈረንሳይ በሩብ ፍፃሜው ኖርዌይን 2ለ1 አሸንፋ ነው ለግማሽ ፍፃሜው የበቃችው።
ሞሮኮ ከፈረንሳይ ጋር የሚያደርጉት ወሳኝ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ የፊታችን ረቡዕ ምሽት 5 ሰዓት ላይ ይካሄዳል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
ኤርሊንግ ሀላንድ 50 ጎሎች ላይ ፈጥኖ የደረሰ ተጫዋች ሆነ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታውን ዛሬ ያካሂዳል
የፕሪሚዬር ሊጉ የመክፈቻ ሳምንታት ጨዋታዎች በሀዋሳ እንደሚካሄዱ ተገለፀ