ቀይ መስቀል ማህበር በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ሐብት በማሰባሰብና ማህብረሰቡን በማስተባበር እያበረከተ ያለው ሚና ተኪ የለሌው ነው – የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ
ሀዋሳ: መስከረም 27/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ሐብት በማሰባሰብና ማህብረሰቡን በማስተባበር እያበረከተ ያለው አስተዋዕጾ ተኪ የለሌው ነው ሲሉ የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ ገለጹ፡፡
በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የጂንካ ቀይ መስቀል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በኣሪ ዞን የማህብረሰብ አቀፍ የአባላት ምክክር መደረክ አካሂዷል፡፡
በተለያየ ጊዜ በየትኛውም አደጋዎች ቀድሞ በመድረስ ሰብአዊ ድጋፎችን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር፥ በኣሪ ዞን የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ለማድረግ እንደሚሰራ ዋና አስተዳዳሪው ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጂንካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ጥላሁን ቢሻው ጽ/ቤቱ ከተቋቋመ ከ37 ዓመታት በላይ ከብሔራዊ ማህበር ዋና መሥሪያ ቤት ጀምሮ በተዋረድ በጋራ በመቀናጀት የተለያዩ አደጋዎች በሚከሰቱበት ወቅት ፈጣን፣ በጎና ሰብአዊ ድጋፎችን እያደረገ መቆየቱን አብራርተዋል።
ተቋሙ ከዚህ በፊት ከደቡብ ኦሞ ዞን ጋር በጋራ ተዋቅሮ እየሠራ ቆይቶ በቅርብ ጊዜ ቀድሞ የነበረው ዞን በመንግስት መዋቅር ምክንያት ለሁለት በመከፈሉ ተቋሙ በኣሪ ዞን በተደራጀና በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል በሀላፊነት እንደሚሠራ አመላክተዋል፡፡
በዚህም ከራሳቸው ጀምረው አባል በመሆን የዞኑ ህዝብም የቀይ መስቀል አባል ሆኖ በተለያየ መልኩ የሚገለፅ አደጋ ሲከሰት ሰብአዊ አገልግሎቶችን ማግኘት እንዲችሉ በሀላፊነት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል ።
ተቋሙ ቋሚ የገቢ ምንጭ ኖሮት ራሱን እንዲችል መሥራትን እንደሚጠይቅም ተገልጿል ።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ለኢትዮጵያውያን ዕድል ነው ያሉት በመድረኩ የተገኙት በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የደቡብ ኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ዱንዳ ናቸው።
በሀገሪቱ በሁሉም ቦታ አጋጣሚ በሚከሰቱ አደጋዎች አንዱ ወደ ሌላው በመንቀሳቀስ ሰብአዊ ድጋፎችን የመስጠት ሀላፊነት በመኖሩ የሚደራጁ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችና ማስተባበሪያ ማዕከላት በዚህ ልክ ይሠራሉ ብለዋል።
ዞኑ አዳዲስ አባላትን በማፍራትና ተጨማሪ በጀት መድቦ ማህበሩ በተሻለ መልኩ መሥራት እንዲችል መደገፍ እንደሚያስፈልግ አቶ ተስፋዬ መልዕክት አስተላልፈዋል ።
በመድረኩ ቀጣይ አባላትን ከማፍራት ጀምሮ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን አጠናክሮ ለማስቀጠል የውል ስምምነትም ተደርጓል።
ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
አቶ ጌታቸው ኬኒ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብሄረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ሆነው ተሾሙ
ባለፉት ጊዜያት በህዝብና በመንግስት መካከል ያለውን ግንኙነት ያጠናከሩ ተግባራት መከናወናቸውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ገለጸ
የኮሪደር ልማት ሥራ ከተማን ዉብ፣ ሳቢና ለነዋሪዎች ምቹ ከማድረግ ባለፈ ለበርካታ ወጣቶች ሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን የዳዉሮ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ አስታወቀ