በአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር በመንግሥት እና በህብረተሰብ ተሳትፎ ከ59 ሚሊዮን 7 መቶ ሺህ ብር በላይ ወጪ የተገነቡ ትምህርት ቤቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ

በአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር በመንግሥት እና በህብረተሰብ ተሳትፎ ከ59 ሚሊዮን 7 መቶ ሺህ ብር በላይ ወጪ የተገነቡ ትምህርት ቤቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ

‎በትምህርት ቤቶቹ መገንባት የአካባቢው ነዋሪና ተማሪዎች ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በ‎አርባምንጭ ከተማ አስተዳደር የጊዞላ መንደር ቅድመ መደበኛ እና 1ኛና መካከለኛ ደረጃ እንዲሁም በልማት ወዜ ቀበሌ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ተመርቀው በይፋ ስራ ጀምረዋል፡፡

‎የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ መስፍን መንዛ (ዶ/ር) የትምህርት ስራ ለሀገር ልማት ወሳኝ በመሆኑ አንደ ከተማ አስተዳደር ተደራሽነቱንና ጥራቱን ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

‎የተመረቁት ትምህርት ቤቶች የህዝብ ጥያቄን መሰረት በማድረግ እቅዱን በመንግስትና በህዝብ ተሳትፎ አሳክተን አስመርቀናል ቀሪ ስራዎችንም እንደዚሁ ተቀናጅተን ለማሳካት ጥረት እናደርጋለን ነው ያሉት፡፡

‎የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ መንዛ፤ ዜጎች በአቅራቢያቸው የመማር እድል እንዲያገኙ ከማድረግ አንፃር የዛሬው ስራ የሚያበረታታ ነው ብለዋል፡፡

‎በተለይም ይላሉ አቶ መለሰ፤ የጊዞላ አካባቢ ተማሪዎች እስከ ሼቻ እየሄዱ ይንገላቱ የነበሩበትን ችግር እንደሚቀርፍ ተናግረዋል፡፡

‎በሁለቱም ቀበሌያት የተመረቁ ትምህርት ቤቶች 54 ሚሊዮን 790 ሺህ 325 ብር ወጪ እንደተደረገበትም አክለዋል፡፡

‎የጊዞላ መንደር ወ/ሮ አስቴር አጪዳና አቶ መስፍን ዳቴ፤ ትምህርት ቤቱ በመገንባቱ የልጆቻቸው ችግር ስለተቀረፈ ደስታቸውን ገልፀዋል፡፡

‎የልማት ወዜ ቀበሌ ነዋሪ አቶ መለሰ መንጁራ፤ ልጆች መንገድ ሲያቋርጡ በመኪና አደጋ እንዲሁም በጎርፍ ይቸገሩ እንደነበር አውስተው ይህ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት በመገንባቱ ደስተኛ ነኝ ይላሉ፡፡

‎የጊዞላ ትምህርት ቤት ተማሪዎችና መምህራንም ስሜቶቻቸውን በደስታ ገልፀዋል፡፡

‎ዘጋቢ፡ ብርሀኑ ዳሾ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን