በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የመደመር ትዉልድ መጽሐፍ ሽያጭ የጥያ ዓለም አቀፍ መከነ ቅርስ ማልማትና ማስፋፊያ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ የማኖር ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ነዉ

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የመደመር ትዉልድ መጽሐፍ ሽያጭ የጥያ ዓለም አቀፍ መከነ ቅርስ ማልማትና ማስፋፊያ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ የማኖር ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ነዉ

ሀዋሳ፡ መስከረም 24/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የመደመር ትዉልድ መጽሐፍ ሽያጭ የጥያ ዓለም አቀፍ መከነ ቅርስ ማልማትና ማስፋፊያ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ የማኖር ስነ-ስርዓት ዓለም አቀፍ ቅርሱ በሚገኝበት ጥያ እየተካሄደ ነዉ።

በመርሃ ግብሩ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንዳሻዉ ጣሰዉ፣ የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋጤ ሰርሞሎ፣ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ(ዶ/ር)፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ኤርሲኖ አቡሬ እንዲሁም ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ዘጋቢ፡ ድልነሳው ታደሰ