ለመላው የኦሮሞ ህዝብ እንኳን የምስጋና፤ የሰላም እና የአንድነት ተምሳሌት ለሆነው የኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን! – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ለመላው የኦሮሞ ህዝብ እንኳን የምስጋና፤ የሰላም እና የአንድነት ተምሳሌት ለሆነው የኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን! – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ለመላው የኦሮሞ ህዝብ እንኳን የምስጋና፤ የሰላም እና የአንድነት ተምሳሌት ለሆነው የኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን! ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ መልካም ምኞታቸውን ገለጹ፡፡

የገዳ ሥርዓት አንዱ አካል የሆነው የኢሬቻ በዓል በኦሮሞ ህዝብ ባህል፤ እምነትና ማንነት ልዩ ስፍራ ያለው፤ ጥልቅ የሆኑ ማህበራዊና ምጣኔሃብታዊ እሴቶችን ያቀፈ፤ በአብሮነትና በአንድነት በድምቀት የሚከበር ታላቅ የምስጋና በዓል ነው፡፡

ባህላዊ ሥርዓቱንና ትውፊቱን ጠብቆ የሚከበረው የኢሬቻ በዓል፤ ከፈታኙ የክረምት ጭጋግና ጨለማ ወደ ብርሃናማው ፀደይ ላሸጋገረ፤ ልምላሜና ብሩህ ተስፋን ላጎናጸፈ ፈጣሪ በኅብረት ወደ መልካ ተወጥቶ ምስጋና በማቅረብ የሚከበር የመሻገርና የብሩህ ተስፋ ምልክት ነው፡፡

ኢሬቻ የሰላምና የወንድማማችነት መገለጫም በመሆኑ የኦሮሞ ህዝብ ከሌሎች ህዝቦች ጋር በጋራ የሚያከብረው፣ አብሮነትና ወንድማማችነት የሚጎለብትበት፣ ህብረ-ብሔራዊነት የሚያብብበት፣ ዕርቅና ይቅርታ ወርዶ ሰላም የሚነግስበት እና የህዝቦች ትስስር ይበልጥ የሚጠናከርበት ታላቅ በዓል ነው፡፡

የኢትዮጵያ የንጋት ዘመን ብስራት የሆነው ታላቁ የህዳሴ ግድብን በተባበረ ክንድ በድል አጠናቀን የላቀ ኢኮኖሚያዊና ስትራቴጂካዊ ጠቄሜታ ያላቸውን ሀገር አሻጋሪ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች በጀመርንበት በዚህ ታሪካዊ ወቅት የሚከበረው የዘንድሮ የኢሬቻ በዓል ከመቼውም ጊዜ በላይ ኅብረት ትብብራችንን አጠናክረን አይቀሬ የሆነው የሀገራችንን ብልጽግና ለማረጋገጥ የምንነሳበት ሊሆን ይገባል፡፡

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነትና የአንድነት እንዲሆንልን መልካም ምኞቴን ለመግለጽ እወዳለሁ!!

ፈጣሪ ሀገራችንና ሕዝቦቿን ይባርክ!

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ