ዌስትሀም ዩናይትድ አሰልጣኝ ግራሃም ፖተርን አሰናበተ

ዌስትሀም ዩናይትድ አሰልጣኝ ግራሃም ፖተርን አሰናበተ

የእንግሊዙ ክለብ ዌስትሃም ዩናይትድ ዋና አሰልጣኙን ግራሃም ፖተርን ከሀላፊነት አሰናብቷል።

አሰልጣኝ ግራሃም ፖተር በምስራቅ ለንደኑ ክለብ ያስመዘገቡት ደካማ ውጤት ለስንብት እንደዳረጋቸው ተገልጿል።

ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ መዶሻዎቹን በሃላፊነት የተረከቡት የ50 ዓመቱ አሰልጣኝ 25 ጨዋታዎችን መርተው 6 ጨዋታዎችን ሲያሸንፉ በ14 ጨዋታዎች ተሸንፈው በ5 ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ወጥተዋል።

 ዌስትሃም በዚህ ዓመት 5 የፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታዎችን አከናውኖ አንድ ጨዋታ ብቻ በማሸነፍ በ3 ነጥብ 19ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ዌስትሃም ዩናይትድ በቀጣይ በቅርቡ ከኖቲንግሃም ፎረስት ሀላፊነት የተነሱትን አሰልጣኝ ኑኖ ስፕሪቶ ሳንቶን ለመሾም በማሰብ ላይ እንደሚገኝ ተነግሯል።

እንግሊዛዊው አሰልጣኝ ግራሃም ፖተር ከዚህ ቀደም ብራይተንን እና ቼልሲን ማሰልጠናቸው ይታወሳል።

ዘጋቢ፦ሙሉቀን ባሳ