“ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያውያን ዳግማዊ ዓድዋ ነው” – በቦንጋ ከተማ የድጋፍ ሰልፍ ተሳታፊዎች

“ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያውያን ዳግማዊ ዓድዋ ነው” – በቦንጋ ከተማ የድጋፍ ሰልፍ ተሳታፊዎች

“ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያውያን ዳግማዊ ዓድዋ ነው” ሲሉ በቦንጋ ከተማ የድጋፍ ሰልፍ ተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቁን አስመልክቶ በቦንጋ ከተማ ክልላዊ የማጠቃለያ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል፡፡

በሰልፉ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የፀጥታ አካላትን አነጋግረናል፡፡

ህዳሴ ግድቡ ለኢትዮጵያውያን ዳግማዊ ዓድዋ ነው ሲሉ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡

የግድቡ መጠናቀቅ የዘመናት ቁጭታችን መቋጫና የኢትዮጵያዊነት ማረጋገጫ ነው ብለዋል፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ ከድህነት የምትወጣበትና በጨለማ ውስጥ ለነበሩ ህዝቦች ብርሀን የሚሆን ነው ብለዋል፡፡

ከ14 ዓመታት የግንባታ ጊዜ ቆይታ በኋላ ግድቡ በመጠናቀቁ መደሰታቸውን አስተያየት ተሰጪዎቹ ገልጸዋል፡፡

ግድቡ የእንችላለን መንፈስን በተግባር ያስመሰከረና ሌሎች ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ለማከናወን አቅም የፈጠረ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ፡ ዳንኤል መኩሪያ – ከቦንጋ ጣቢያችን