“ህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን ጅማሮ ምልክት ነው” – ሰልፈኞች
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅን አስመልክቶ በቦንጋ ከተማ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፡፡
ያነጋገርናቸው የሰልፉ ተሳታፊዎች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተጠናቆ ለምረቃ በመብቃቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
ለግድቡ ግንባታ ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሰው፤ ግድቡ ለኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን ጅማሮ ምልክት ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ ያለው ትርጉምና አንደምታ ልዩ ነው ሲሉም ነው የገለጹት፡፡
በድጋፍ ሰልፉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የስድስቱም ዞኖች አስተዳዳሪዎች፣ ከወረዳና ከከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡
ዘጋቢ፡ ዳንኤል መኩሪያ – ከቦንጋ ጣቢያችን
More Stories
“ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የህብረታችን አርማ የብልጽግናችን አሻራ ነው” – ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር)
የጉራጌ ዞን የጸጥታ ምክር የ2017 ዓ.ም የማጠቃለያ ጉባኤ እያካሄደ ነው።
“የባህል ልማታችን ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን” በሚል መርህ 10ኛው ዙር የከምባታ ዞን ሕዝቦች የባህል፣ ታሪክ፣ ቋንቋ እና ልማት ሲምፖዚየም በዱራሜ እየተካሄደ ነው