ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተጠናቆ መመረቁን አስመልክቶ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቦንጋ ከተማ የድጋፍና የደስታ መግለጫ ሰልፍ እየተካሄደ ነው
የግድቡ ግንባታ በድል እንዲጠናቀቅ መንግስት የወሰደውን አቋም የሚደግፉ መፈክሮችን የያዙ ሰልፈኞች ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ቦንጋ ከተማ ገብተዋል።
“በኅብረት ችለናል” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ባለው የድጋፍና ደስታ መግለጫ በሆነው በዚህ ሰልፍ ላይ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያንን የዘመናት ቁጭት የመለሰ ነው፣ ሕዳሴ ግድብ የአንድነትና የጽናት ውጤት ማሳያ ነው፣ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ጅማሮ ምልክት ነው፣ ህዳሴ ግድብ የከበረ በላብ የታሰረ፣ ግድባችን የህብረ ብሔራዊነታችን እና የአንድነታችን መሰረት የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን ሰልፈኞቹ በአደባባይ እያሰሙ ነው።
የድጋፍ ሰልፉ በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ሲደረግ ቆይቶ ዛሬ ክልላዊ ማጠቃለያው በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
ዘጋቢ፡ አሳምነው አትርሳው – ከቦንጋ ጣቢያችን

More Stories
ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የሚወጡ ተመራቂ ሰልጣኞች በሰለጠኑበት ዘርፍ ሀገሪቱ ለጀመረችው የብልጽግና ጉዞ የድርሻቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው ተገለጸ
ለትውልድ ግንባታ መሠረት ለሆነው የሞዴል ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ትኩረት ተሰጥቶ ሊሠራ ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር)
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን ምሁር-አክሊል ወረዳ በመንግስትና በህብረተሰቡ የተከናወኑ የተለያዩ የልማት ሥራዎች የምረቃ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው