በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ አስተዳደር ሁለት ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቁ ዘመናዊ ሆቴሎችን ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ
ዓለም አቀፍ ሆቴሎቹ አብዮት አገዘ እና ጴጥሮስ ጀጎ በተባሉ የግል ባላሃብቶች የሚገነቡ መሆናቸውም በዚህ ወቅት ተመላክቷል።
የግንባታ የመሠረት ድንጋዩን የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር ዝናቡ ወልዴ እና የዲላ ከተማ የሥራ ኃላፊዎች በጋራ ያስቀመጡ ሲሆን የሆቴሎቹ መገንባት በከተማው የሆቴል ኢንዱስትሪውን የሚያሳድግ መሆኑም ተጠቁሟል።
ሆቴሎቹ ተገንብተው ሲጠናቀቁ ዓለም አቀፍ የጥራት መለኪያዎችን በሟሟላት አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩም ተነግሯል።
ይኸውም በሆቴል ቱሪዝም ዘርፍ የታቀደውን ዕቅድ በማሳካት የከተማውን ዕድገትና ልማት ለማፋጠን ብሎም ተወዳዳሪነቱን የሚያረጋግጥ መሆኑንም ነው ዶክተር ዝናቡ ወልዴ ያብራሩት።
ሆቴሎቹን በአጭርና በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ ዞኑና ከተማ አስተዳደሩ በጋራ በመቀናጀት ተገቢውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርጉም ተገልጿል።
የዲላ ከተማን ሞዴልና ተመራጭ ማዕከል ከማድረግም በላይ ለነዋሪዎቿ ምቹ የመኖሪያ ሥነምሕዳር ለመፍጠር ሌሎች በኢንቨስትመንት ዘርፍ የሚሰማሩ የግል ባለሀብቶችን ለመጋበዝ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች በመሠራት ላይ እንደሚያገኙም ተብራርቷል።
ዘጋቢ:- እስራኤል ብርሃኑ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
መሬት ውስን የተፈጥሮ ሀብት በመሆኑ በአግባቡ በመምራትና ከብክነት በመጠበቅ ቀጣይነት ያለዉን ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
መስቀል የድህነት ምልክት መሆኑን የካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮና ምዕራብ ኦሞ አህጉረ-ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ህዝቅኤል ተናገሩ