በጎፋ ዞን 5ኛ ዩኒየን የሆነዉ የቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ዩኒየን መሰራች ኮሚቴ መድረክ በሳዉላ ከተማ ተካሄደ
የህብረት ሥራ ማህበራት ማህበራዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን የጎፋ ዞን ህብረት ሥራ ጽ/ቤት ገልጿል።
የቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ዩኒየን መስራች ኮሚቴ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የጎፋ ዞን ህብረት ሥራ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብረሃኑ ደቻሳ፤ በዞኑ ካለዉ ህዝብ ቁጥር አንፃር በህብረት ሥራ ማህበር ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱት ከ16 ሺህ የማይበልጥ ህዝብ መሆኑን ተናግረዋል።
አክለውም በዞኑ ከ150 የማይበልጡ ህብረት ሥራ ማህበራት መኖራቸዉን አሰታዉሰዉ፤ የዞኑን ህዝብ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግ በርካታ አዲስ ህብረት ሥራ ማህበራትንና ዩኒየኖችን መፍጠር እንዳለባቸው ገልፀዋል።
የኑሮ ዉድነቱን በማረጋጋት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ በህብረት ሥራ ማህበራት ተደራጅቶ መንቀሳቀስ አማራጭ የሌለዉ ጉዳይ መሆኑን አቶ ብረሃኑ አሳስበዋል።
አሁን እየተደራጀ ያለዉ የቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ዩኒየን የአባላቱን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ከማሳደግ ባለፈ በሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ላይ የራሱን አሻራ ለማኖር ውጤታማ ስልት ቀይሶ እንዲሰራ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
የህብረት ሥራ ማህበራት አደረጃጀት መመሪያ ቁጥር 896/2014 ዙሪያ ለመስራች ኮሚቴዎች ማብራሪያ የሰጡት የዞኑ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት የህብረት ሥራ ማህበራት ማደራጃና ማስፋፊያ ቡድን መሪ አቶ ወንዱ ደበበ፤ የቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ዩኒየኑ በዉስጡ 27 ማህበራትን ያቀፈ ሲሆን ለበለጠ ዉጤታማነት ይሰራል ብለዋል።
የመሰራች ዩኒየን አባል ከሆኑ ማህበራት የዛሎ ማሶና የሳዉላ ከተማ መምህራና ሠራተኞች ገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህራት በአብነት ተጠቅሰዋል።
የዩኒየኑን ስያሜ፣ መተዳደሪያ ዉስጠ ደንብና ተያያዥ ጉዳዮችን የሚያዘጋጁ አምስት የመስራች ኮሚቴ አባላት ምርጫ በማድረግ መድረኩ ተጠናቋል።
ዘጋቢ፡ መንግስቱ ታሪኩ – ከሳዉላ ጣቢያችን

More Stories
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ እና የአደረጃጀት ዘርፍ የ2018 በጀት አመት አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዕቅድ ዙሪያ በታርጫ ከተማ ውይይት እየተካሄደ ነው
ኦሞ ባንክ ሳውላ ዲስትሪክት በ2018 በጀት ዓመት ከ86 ሚሊዮን ብር በላይ የተጣራ ቁጠባ ማስመዝገቡን ገለጸ
እየተካሔደ ያለው ሀገራዊ ምክክር በሀገሪቱ አንድነት እና ሠላም ለማስፈን ፋይዳው የጎላ መሆኑን የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ