ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መመረቁን ተከትሎ “በህብረት ችለናል” በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይት መድረክ በጂንካ ከተማ ተካሄደ
ሀዋሳ፡ መስከረም 07/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መመረቁን ተከትሎ “በህብረት ችለናል” በሚል መሪ ቃል የኣሪ ዞን አስተዳደር የጂንካ ክላስተር ክልል ተቋማት በጋራ ያዘጋጁት የፓናል ውይይት መድረክ በጂንካ ከተማ እየተካሄደ ነው።
ፈተናዎችን በብልጠት በመሻገር ለስኬት በቅተናል ሲሉ መድረኩን በንግግር የከፈተቱት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ፀሐይ ወራሳ ገልፀዋል።
የዛሬው ትውልድ ነገ የተሻለች ኢትዮጵያን ለማስረከብ ጠንክሮ መሥራት አለበት ሲሉም ወ/ሮ ፀሐይ አሳስበዋል።
የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ በበኩላቸው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የብሔራዊ ኩራታችን አርማ፣ በአለም አደባባይ ጀምረን መጨረስ እንደሚንችል ተምሳሌታችን ነው ብለዋል።
በቀጣይ ግዙፍ የልማት ውጥኖችን ለማሳካት ከህዳሴ ግድብ ትልቅ ትምህርት የተወሰደበትም ነው ሲሉ ዋና አስተዳዳሪው ገልፀዋል።
ግድቡ በድል ተጠናቅቆ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ በመግባቱ እንኳን ደስ አለን መልዕክትም አስተላልፈዋል ።
ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
መሬት ውስን የተፈጥሮ ሀብት በመሆኑ በአግባቡ በመምራትና ከብክነት በመጠበቅ ቀጣይነት ያለዉን ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
መስቀል የድህነት ምልክት መሆኑን የካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮና ምዕራብ ኦሞ አህጉረ-ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ህዝቅኤል ተናገሩ