የሴቶች የ3 ሺ ሜትር መሰናክል ፍፃሜ በዛሬዉ ዕለት ይካሄዳል

የሴቶች የ3 ሺ ሜትር መሰናክል ፍፃሜ በዛሬዉ ዕለት ይካሄዳል

በቶኪዮ እየተካሄደ በሚገኝው 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሴቶች የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ፍፃሜ በዛሬዉ ዕለት ይካሄዳል፡፡

ከቀኑ 9 ሰዓት ከ55 ደቂቃ ላይ በሚካሄደዉ የሩጫ ዉድድር ኢትዮጵያ በሁለት አትሌቶች ትወከላለች፡፡

ማጣሪያዉን በጥሩ ዉጤት ማለፍ የቻሉት አትሌት ሲምቦ ዓለማየሁ እና ሎሚ ሙለታ ኢትዮጵያን በመወከል የሚወዳደሩ አትሌቶች ናቸዉ፡፡

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ