አትሌት ፍሬወይኒ ሃይሉ በሜዳልያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት አልቻለችም
በቶኪዮ እየተካሄደ በሚገኘው 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 1500 ሜትር ፍፃሜ ውድድር ላይ የተካፈለችው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፍሬወይኒ ሃይሉ ሜዳልያ የሚያስገኝ ደረጃን ይዛ አላጠናቀቀችም።
አትሌቷ 6ኛ ደረጃን ይዛ ነው ያጠናቀቀችው።
ውድድሩን ኬንያዊቷ አትሌት ፌይዝ ኪፕየጎን ቀዳሚ ሆና በማጠናቀቅ ለአራተኛ ተከታታይ ጊዜ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለሀገሯ የወርቅ ሜዳልያ አስገኝታለች።
ሌላኛዋ ኬንያዊት አትሌት ዶርከስ ኤዎይ 2ኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ የብር ሜዳልያ ስታሸንፍ አውስትራሊያቷ አትሌት ጄሲካ ሀል ውድድሩን በ3ተኛነት አጠናቃለች።
በሻምፒዮናው 6 የፍፃሜ ውድድሮችን ያከናወነችው ኢትዮጵያ እስካሁን የወርቅ ሜዳልያ ማግኘት አልቻለችም።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
የባርሴሎና ቀዳሚ ተመራጭ
ጤናማ እና አምራች ዜጋን ለመፍጠር በጤና ስፖርት ቡድኖች የሚሳተፍ ማህበረሰብ መገንባት ወሳኝ መሆኑን የጎፋ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ገለጸ
ማንቸስተር ሲቲ የፊል ፎደን ውል ለማራዘም ስራ መጀመሩ ተገለፀ