ሙያዊ ስነ-ምግባር የተላበሰ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋዩን እርካታ ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ
ሀዋሳ፡ መስከረም 06/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ሙያዊ ስነ-ምግባር የተላበሰ አገልግሎት በመስጠት በፍትህ ዘርፍ የተገልጋዩን እርካታ ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ገለጸ፡፡
የጉራጌ ዞን ፍትህና ፖሊስ መምሪያ በታክቲክና ቴክኒክ ወንጀል ምርመራ ዙሪያ ለስር መዋቅር ፖሊስና ዐቃቢያነ ህግ ከመስከረም 6-7/2018 ዓ.ም ግንዛቤ ለመስጠት የተዘጋጀ የስልጠና መድረክ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ነው።
የጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ኤልያስ ሰብለጋ በመክፈቻ ንግግራቸው ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም በርካታ ወንጀሎች የሚፈፀሙ በመሆኑ ይሔንን ለመግታት የፖሊስና የዐቃቢያነ ህግ ክህሎትና አቅም ማሳደግ ይገባል ብለዋል።
በየቦታው የተለያየ መጠን ያላቸው የትራፊክ አደጋዎች እንደሚከሰቱ የገለፁት ሃላፊው ይህንን አደጋ በሳይንሳዊ መንገድ ምርመራ በማድረግ ለውሳኔ ማቅረብ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የቴክኒክና የታክቲክ ምርመራ ከጊዜው ጋር አብሮ በሚሔድ መልኩ ስልጠና መስጠት በፍትህ ዘርፍ ላይ አይነተኛ ለውጥ ያመጣል ሲሉ አቶ ኤልያስ ተናግረዋል።
አክለውም የሚፈለገውን አገልግሎት መስጠት እንዲቻል ለህብረተሰቡ የሙያን ስነ-ምግባር በተላበሰ ሁኔታ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ ገልፀዋል።
ስልጠናው ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል።
ዘጋቢ፡ ፍስሃ ክፍሌ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
ታላቁ የህዳሴ ግድብ ተጠናቆ መመረቅን ምክንያት በማድረግ የይርጋጨፌ ወረዳ እና ከተማ አስተዳደር በጋራ በመሆን የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ
የካፋ ዞን ጤና መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2018 ዕቅድ ዝግጅት ላይ ውይይት እያካሄደ ነው
በወላይታ ዞን አረካ ከተማ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቁን ተከትሎ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ