በወላይታ ዞን አረካ ከተማ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቁን ተከትሎ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ
ሀዋሳ፡ መስከረም 06/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ በመመረቁ የወላይታ ዞን አረካ ከተማ ነዋሪዎች የተሰማቸውን ደስታ በህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በመግለጽ ላይ ናቸው።
በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአረካ ከተማ ከንቲባ ጥበቡ ሳሙኤል፥ አፍሪካውያን ታላላቅ መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት የምዕራባውያንና ሌሎች አበዳሪና ድጋፍ ሰጪ ተቋማትን ሲማጸኑ መኖራቸውን ገልጸው፥ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በህዝቦቿ ጥረት መገንባቱ በራስ አቅምና ተነሳሽነት ትርጉም ያላቸውን ታላላቅ ፕሮጀክቶችን አቅዶ እውን ማድረግ እንደሚቻል ትምህርት የሰጠና እንደ ሀገር ትልቅ መሰረት የጣለ መሆኑ ተናግረዋል፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለአገራችን ህዝብ የይቻላል መንፈስን ያላበሰ፣ የዳግም አድዋ ድላችን ብስራት፣ አገራዊ መግባባት ፈጥሮ የሁሉንም ህዝብ አሻራ በማኖር ያለቀ ግዙፍ ፕሮጀክት መሆኑ ጠቀሰዋል፡፡
አባይ ውሀ ብቻ አይደለም ያሉት ደግሞ የከተማው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘለቀ ዛራ፥ አባይ የኤሌትሪክ ኃይል እንዲሁም የኢኮኖሚ ምንጭ በመሆኑ የህዳሴ ግድባችን የአባይ ዘመን ትውልድ አኩሪ ገድል የሚዘከርበት አሸናፊነት አርማ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በቀጣይ ኢትዮጵያ የባር በር እና በራሷ ታሪካዊ ወደብ ተጠቃሚ እንድትሆን በጋራ በመተባበር መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
ከውጭም ሆነ ከውስጥ በሚነሱ የተለያዩ ፈተናዎች ሳንበገር ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በሰላም ማጠናቀቃችን አንድነት ኃይል መሆኑን አሳይቷል ያሉት የሰልፉ ታዳሚዮች መካከል ወ/ሮ ወርቄ አበበና አቶ ደባልቄ ኦርታቦ ናቸው።
ዘጋቢ፡ ድርሻዬ ጋሻው – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎችን ተጠቅሞ በመስራት ከህገወጥ ስደትና ከድህነት መላቀቅ እንደሚገባ ተገለጸ
በራሳቸው የሚተማመኑ፣ በሥራ ክቡርነት የሚያምኑ፣ የሙያና ክህሎት ብቃት ያላቸውን የሰው ኃይል መፍጠር ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ
የኮሌጁንና የአካባቢውን ማህበረሰብ በቴክኖሎጂ የማስተሳሰር ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ