የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ሴክተር ጉባኤውን በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ነው

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ሴክተር ጉባኤውን በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ነው

‎በሴክቶሪያል ጉባኤው በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማትና ኢንዱስትሪ ክላስተር አስተባባሪ እና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ወልደሚካኤል፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርናና ገጠር ክላስተር አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ዑስማን ሱሩር፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መሐመድ ኑርዬ፣ የብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ፣ የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ መነቴ ሙንዲኖ ታድመዋል።

‎ከፌደራል፣ ከክልል፣ ከዞን፣ ከልዩ ወረዳ እና ከከተማ አስተዳደር የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛል።

‎ዘጋቢ: አብደላ በድሩ