በወንዶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ድል አልቀናቸውም
በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በወንዶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ፍፃሜ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የሜዳልያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት ሳይችሉ ቀርተዋል።
በውድድሩ ኢትዮጵያ በአትሌት ለሜቻ ግርማ፣ ሳሙኤል ፍሬው እና ጌትነት ዋለ ተወክላ ነበር።
ሆኖም ግን ርቀቱን ሳሙኤል ፍሬው 4ኛ፣ ለሜቻ ግርማ 6ኛ እንዲሁም ጌትነት ዋለ 14ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።
ውድድሩን ኒውዚላንዳዊው አትሌት ጆርጅ ቤሚሽ የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ ሆኗል፡፡
ሞሮካዊው አትሌት ሶፊያን ኤልባካሊ 2ኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ ኬንያዊው አትሌት አድመንድ ሴሪም 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
የባርሴሎና ቀዳሚ ተመራጭ
ጤናማ እና አምራች ዜጋን ለመፍጠር በጤና ስፖርት ቡድኖች የሚሳተፍ ማህበረሰብ መገንባት ወሳኝ መሆኑን የጎፋ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ገለጸ
ማንቸስተር ሲቲ የፊል ፎደን ውል ለማራዘም ስራ መጀመሩ ተገለፀ