ተጠባቂው የማንቹሪያን ደርቢ አመሻሽ 12 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ላይ ይካሄዳል

በ4ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ መርሐግብር ተጠባቂው የማንቹሪያን ደርቢ ከደቂቃዎች በኋላ በማንቸስተር ሲቲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ መካከል በኤቲሐድ ስታዲየም ይካሄዳል።

የአዲሱ የውድድር ዓመት ጅማሮ ያላማረላቸው ሁለቱ የማንቸስተር ከተማ ክለቦች ወደ ትክክለኛ የውጤታማነት ሀዲድ ውስጥ ለመግባት የሚያከናውኑት ወሳኝ ፍልሚያ ነው።

በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመራው ማንቸስተር ሲቲ በመጀመሪያ ሳምንት መርሐግብር ምንም እንኳን ዎልቭስን 4ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ አዲሱን የውድድር ዓመት በድል ቢጀምርም ባለፉት ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች በቶትንሃም እና በብራይተን መሸነፉ ይታወሳል።

በዚህም ክለቡ በፕሪሚዬር ሊጉ ከመጀመሪያዎቹ ሦስት ጨዋታዎች ሁለቱን በመሸነፍ ከ20 ዓመታት በኋላ ደካማ ጅማሮን በማድረግ ላይ ይገኛል።

በአሰልጣኝ ሩበን አሞሪም የሚመራው ማንቸስተር ዩናይትድ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ጨዋታዎች ሙሉ ሶስት ነጥብ ማግኘት ቢሳነውም በ3ኛ ሳምንት መርሐግብር በሜዳው በርንሌይን 3ለ2 በሆነ ውጤት ከተሸነፈ በኋላ ሊጉ ለሀገራት ጨዋታ መቋረጡ ይታወሳል።

ሲቲዝኖቹ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ እንዲሁም ከ2021 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከከተማ ባላንጣቸው የተሻለ ደረጃ ላይ መቀመጥ የቻሉት ቀያይ ሰይጣኖች ደግሞ አሸናፊነታቸውን ለማስቀጠል ይፋለማሉ።

ማንቸስተር ዩናይትድ በ3 ጨዋታ 4 ነጥቦችን በመሰብሰብ 11ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ማንቸስተር ሲቲ በበኩሉ በ3 ነጥብ 17 ደረጃን ይዟል።

በምሽቱ ጨዋታ በማንቸስተር ሲቲ በኩል ራያን አይት ኑሩ፣ ራያን ሼርኪ እና ኦማር ማርሙሽ በጉዳት ለጨዋታው አለመድረሳቸው የተረጋገጠ ሲሆን ጆን ስቶንስም መሰለፉ አጠራጣሪ መሆኑ ተገልጿል።

በማንቸስተር ዩናይትድ በኩል ደግሞ ማቲያስ ኩኛ፣ ማሰን ማውንት እና ዲያጎ ዳሎ በጉዳት ምክንያት የደርቢው ጨዋታ እንደሚያመልጣቸው ክለቡ አሳውቋል።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ